Tuesday, December 27, 2016

ከውስጥ አዋቂ የተላከ – “የኮማንድ ፖስቱ የስራ ውጤቶች እየታየ ነው”

ከውስጥ አዋቂ የተላከ
*********************
ለሁሉም የመገናኛ ብዙሀን ብታስተላልፉልን፡፡
=============================
“የኮማንድ ፖስቱ የስራ ውጤቶች እየታየ ነው”
“ማሰልጠኛ” በሚል በደቡብ ክልል አላጌ ወታደር ማሰልጠኛ ህዘቡን አጉሮ ያቆዮበት ቦታ የተከናወኑትን ምሳሌ የሚሆኑ ተግባሮች እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡
ከታጎሩት ሰዎች መካከል፡-
XXX – እድመያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 91 ህፃናት በማጎሪያ ጣቢያው በወታደራዊ ምርመራ እና ቅጣት ስሰቃዩ ቆይተው ለመፍታት አንድ ሳምንት ስቀራቸው ተለይተው ለብቻ ዶርም እንዲሰጣቸው ከተደረገ በኋላ አሁን ተለቀዋል፡፡
XXX – እድመው 85 አመት የሚሆነው አቶ ቡልቻ ሶረሳ የተባሉ ሽማግሌ ከጉጂ (ዱግዳ ዳዋ) የተያዘ በማጎሪያ ካምፑ ስሰቃዩ ቆይተው አሁን ተለቀዋል፡፡
XXX – እድመው 35 አመት የሚሆነው አብዱሰመድ ገፎ የተባለ ወጣት ከመዳ ወላቡ የተያዘ በድብደባ ተጎድቶ አ.አ ፖሊስ ሆስፕታል ከሄደ በኋላ መሞቱን አረጋግጠናል፡፡
XXX – እድመያቸው 65 አመት የሚሆናቸው ሁለት አሮግቶች ወ/ሮ ፍታሌ በዳዳ ከቦሰት እና ወ/ሮ መሙና ዳጋጎ ከአዳሚ ቱሉ በማጎሪያ ካምፑ ስሰቃዩ ቆይተው ተለቀዋል፡፡
XXX – እድመዋ 35 አመት የሚሆናት ወ/ሮ ሻዋዬ በዳዳ ከቦሰት በሏን ስያጡ የተያዘች በጤና ታመው በማጎሪያ ጣብያው በወታደራዊ ምርመራና በበሽታ ስሰቃዩ ቆይታ ተለቃለች፡፡
XXX – አንዲት ሴት ከሰበታ የተያዘች ከ2 ዓመት ህፃን ጋር ታስራ ስትሰቃይ ቆይታ ተለቃለች፡፡
XXX – በርካታ አካል ጉዳተኛ ዜጎችም በማጎሪያ ጣቢያው ስሰቃዩ እንደነበር የአይን ምስክርነተን እሰጣለሁ፡፡
XXX – በካምፑ ውስጥ ስፈፀሙ ከነበሩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል በጥበቃ ወታደሮች ወዳ ሽንት ቤት ሲሄዱና ስመለሱ እንዲሁም ወደ ምግብ ቤት ሲሄዱ፤ ስመገቡና ከዚያ ስመለሱ የሚፈፀመው ድብደባ ለመዝናኛ ካልሆነ በስተቀር ምንም ምክንያት የሚሰጠው አይደለም፡፡
XXX – በካምፑ ውስጥ ስፈፀሙ ከነበሩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል ሌላው ደግሞ በምርመራ ላይ የሚፈፀም ጥፍር ከመንቀል እስከ በእጅ ድርል መብሳት የሚዘልቅ በጭካኔ የተሞላ የማሳመን ተግባር እንደነበር እመሰክራለሁ፡፡
XXXXXX በሌላ በኩል ደግሞ በራሳቸው ፊረጃ “ሀርድ ኮር” ብሎ የመደቡትን እና እስከአሁንም በባሰ ስቃይ ውስጥ የቆዩትን 852 ዜጎች ከዚህ ውስጥ 80 ሴቶች የሚገኙበት በታጎሩበት ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ አስቀርተዋቸዋል፡፡
በቀጣዩ ሌሎች ነገሮችንም ምንጫቸውን አጣርቼ እልክላችኋለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment