Friday, December 16, 2016

ጎንደር – ወያኔ የተዳከመውን ሰራዊት በአዲስ ልትቀይር ነው!


የጎንደር ሕዝብ ትግል ከቋራ እስከ ጃናሞራ!
ወያኔ የተዳከመውን ሰራዊት በአዲስ ልትቀይር ነው!
ሃሙስ ታህሳስ 6 ቀን 2009
እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የመጣው የጎንደር ሕዝብ ትግል ከሱዳን ጠረፍ ከቋራ እስከ ታላቁ ራስ ዳሸን ተራራ ጥግ ጃናሞራ ተዛምቷል። በአርማጭሆ፣ በቆላማው ወገራ፣ በወልቃይት ጠገዴ፣ በመተማና ቋራ በገበሬወች ላይ ሲካሄድ የነበረው ውጊያ ሰሞኑን ወደ ስሜን በኩል ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልጋቸው አዳዲስ ሶስት ግንባሮች ላይ ጦርነት ተከፍቶ ፍልሚያ አለ። የተገፋው ገበሬ እራሱን ለመከላከል እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ እያደረገ ነው።
ግራ የገባው ወያኔ የወረዳ መንገዶችን በኬላ በመዝጋት ፍተሻ እያደረገ ነው። ከጎንደር ሾልኮ የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው ወያኔ ከፍተኛ የአካልና የሞራል ጉዳት የደረሰበትን ጦር አንስቶ በአዲስ ለመተካት እንቅስቃሴ እያደረገ ስለሆነ ጥንቃቄ ይደረግ።
ጭንቅ ውስጥ የገባው ወያኔ ህፃናትን፣ እናቶችንና አረጋዊያንን በመያዣነት አስሮ በግፍ እያንገላታ ነው። ለጊዜው ስማቸውን የማንጠቅሰው የገበሬ ሴት ቤተሰቦች ከ6 አመት ህፃን ጋር ጎንደር ውስጥ በ1ኛ ፖሊስ ጣብያ ታስረው ይገኛሉ። ይህ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት የህዝቡን እልህና ቁጣ እየጨመረው እንደሚገኝ ከቦታው ካናገርናቸው ተረድተናል።
ሙሉነህ ዮሃንስ

No comments:

Post a Comment