Tuesday, December 27, 2016

የሺዓ ጥምር ኃይል የሶርያን ሱኒዎች እየተዋጋ ነዉ ተባለ | ሊደመጥ የሚገባው ዜና ትንታኔ በሳዲቅ አህመድ

ችግሩ የሱኒና የሺአ እንዳይመስል የሱኒ አገራት በፖለቲካዊ ተአርሞ ለጉዳዩ ተገቢ አትኩሮት ሳይሰጡት፤ ኢራናዊዉ የሺአ አብዮት ናይጄሪያ ደርሶል። አህባሽ በሚባል ጭምብል ኢትዮጵያ የገባዉ የሒዝቡላህና የኢራን ቀመር ኢትዮጵያን መረጋጋት ነፍጓል። አህባሽ የሚለዉ መጠሪያ በህዝብ ጥረት በመክሰሙ በህገመንግስታዊ ከለላ ስር የኢራኑ ስሌት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሺአ መጠሪያን ይዞ አንገቱን ቀና እያደረገ ነዉ። በኢራን የሚደገፉትን የየመን የሺአ አማጽያን ስምሪት ለመግታት በሚያስመስል መልኩ የአረብና የሙስሊም አገራት የአስብ ወደብን ተከራይተዉ ሰፍረዋል። ወደ ኢትዮጵያ እየመጣ ያለዉን ፖለቲካዊ ማራቶን ምንጭ ለመቃኘት ወደ ሶር ያ ተጉዘናል።
***
ቢቢኤን ታኅሣሥ 16/2009 
አለዋት በመባል የሚታወቀዉ የሺዓ ቅርንጫፍ እምነት ተከታይና የቃልብያ ጎሳ አባላት የሆኑት የአል አሳድ ቤተሰቦችና የሶርያ ገዥዎች የተነሳባቸዉን ህዝባዊ አመጽ ለመደምሰስ ሁሉም የሺዓ ሐይላት ሶርያ ዉስጥ በመሰባሰብ ሲኒዎችን እየተዋጉ መሆኑን ተንታኞች ያስረዳሉ።
ፈረንሳይ ሶርያን ቅኝ ትገዛ በነበት ወቅት ከቅኝ አገዛዙ ሐይሉ ጋር ወግነዋል ተብለዉ መገለል የደረሰባቸዉ የአለዋት እምነት ተከታዮች በአሁኑ የሶርያ የፕሬዝዳንት አባት ሐፊዝ አል አሳድ አማካኘት ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና መፈንቅለ መንግስትን ተከትሎ በመጋቢት 3/1963  በጃቸዉ የገባዉን ስልጣን ለማስቀጠል ኢራን በበላይነት በምትመራዉ የሺዓ ሐይልና በሩስያ እየተደገፍፉ በሶርያ ሱኒዎች ላይ የሚያደርሱት እልቂት እየከፋ መሆኑ እየተዘገበ ነዉ።
ሒዝቡላህ፡
ለሶሪያ መንግስትና ለኢራን ቅርበት ያለዉ በሐሰን ነስራህ የሚመራዉ ሒዝቡላህ በተለያዩ መንግስታትና በአረብ ሊግ አሸባሪ ተብሎ ይፋዊ መገለል የደረሰብት ቢሆንም፤ በሶሪያ መሬት ላይ በመንቀሳቀስ የሶርያ ሱኒዎች ላይ የከፋ ጭፍጨፋ እያከናወነ መሆኑ እየተዘገበ ነዉ። ሒዝቡላህ በሊባኖስ ዉስጥ እንደፖለቲካ ፓርቲ በህጋዊነት የሚንቀሳቀስ ቢሆንም የጂሃድ መማክርት የሚል የራሱ የሺዓ የጦር ሰራዊት ያለዉና በሊባኖስ መንግስት ላይ እራሱን የጫነ ሌላ መንግስት መሆኑን ተንታኞች ያስረዳሉ።
ሒዝቡላህ ከኢራን ሌላ ከፍተኛና ታላቅ ወታደራዊ ልምምድ ያለዉ የሺአ ሐይልና ከኢራኑ ልዩ ጦር  ቀጥሎ በሺዓዎች ዘንድ ተምሳሊታዊ የሆነ ቦታ ያለዉ መሆኑ ይታወቃል።ሒዝቡላህ 65ሺ ተዋጊ ወታደሮች ያሉት ሲሆን በብቃትና በልምድ ከሊባኖስ የመከላከያ ሰራዊት በተሽሻለ መልኩ ጠንካራ እንደሆነ ይነገራል።በብዙህ ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮቹን ወደ ሶሪያ የላከዉ ሒዝቡላህ ከ1500 በላይ የሚሆኑት ሚሊሻዎቹ ሶርያ ዉስጥ በሱኒ አማጽያን እንደተገደሉበት ቢዘገብም፤ ሒዝቡላህ በሶርያ መሬት ላይ ከሌሎች የሺዓ ሐይላት ጋር ጠንክሮ እየሰራ መሆኑ እየተዘገበ ነዉ።
ጀይሸል መህዲ፡
ዝርያቸዉ ከሊባኖስ እንደሆነ የሚነገረዉ በኢራቁ የሺዓ አስተማሪ ሙቅተዳ አልሳደር የሚመሩት የጀይሸል መህዲ ሚሊሻዎች በሶርያ ዉስጥ የሰፈሩ ሲሆን የሶርያ ሱኒዎችን እንደሚዋጉም በአረብ የመገናኛ ብዙሗን በስፋት ይዘገባል። ሙቅተዳ አልሳደር ተሰሚነት ያላቸዉ የሺዓ መሪ ናቸዉ። የአላሳደር ንቅናቄ በኢራቅ ፖለቲካ ዉስጥ ስር የሰደደ ሲሆን፤ ንቅናቄ የኢራቅን መንግስት ከጀርባ ሆኖ ይሾፍራል ሲሉም ክስ የሚያቀርቡ አሉ።የሙቅተዳ አልሳደር የሺዓ ሚሊሻዎች በኢራቅ ፓርላማ እዉቅናና ደሞዝ የተመበላቸዉና እዉቅና ያላቸዉ የሺዓን የበላይነት ለማስረጽ በገሃድ እንደሚቀሳቀሱ ኢራቃዉያን ሱኒዎች ያስረዳሉ።የሙቅተዳ አልሳደር ሚሊሻዎች ማእከላዊ የሆነ የሺዓ የጦር ሐይልን በሶርያ ዉስጥ እንዲደራጅ ከፍተኛ ሚና ያላቸዉ መሆኑን በመስኩ ጥናት የሚያከናዉኑ አካላት ያስረዳሉ። 
የአብዱል ፋድል አል አባስ ብርጌድ፡
አብዱል ፋድል አል አባስ በመባል የሚታወቀዉ የሺዓ ብርጌድ ሶርያ ዉስጥ ባሉ የሺዓ ሐይላት በግል የተቋቋመ ሲሆን፤ ብርጌዱ ከኢራቅ ወደዉ የተቀላቀሉትን የሺዓ ሚሊሻዎችና ሶርያዉያንን በማሰላፍ ሱኒዎችን እየተዋጋ መሆኑ ይታወቃል።
የሊዋ አል ፋጢሚዩን የጦር ብርጌድ
በኢራን የሚደገፈዉና ኢራን ያስታጠቀቸዉ ሊዋ አልፋጢሚዩን የተባለዉ የአፍጋኒስታን ሺዓዎች የጦር ብርጌድ ሶርያ ዉስጥ የገባ ሲሆን ይኸው ብርጌድ ከሌሎች የሺዓ ሐይላት ጋር በመጣመር የሶርያን ሱኒዎች ይዋጋል። 
የአፍጋኒስታኑ ሊዋ አልፋጢሚዩን ብርጌድ የፕርሺያን ቋንቋ በሚናገሩ አፍጋኒስታዉያን የተዋቀረ ሲሆን፤ አፍጋኒስታን ከሩስያ ጋር ባደረገቸዉ ጦርነት ሳቢያ ወደ ኢራን ተሰደዉ የገቡት ስደተኞች ለብርጌዱ የጀርባ አጥንት እንደሆኑት ይነገራል።በኢራን አልረዳም ሲል የሚክደዉ ሊዋ አልፋጢሚዩን የሰይዳ ዘይነብን መቃብር እንጥብቃለን በሚል የሺዓ ተልእኮ ሁለት ሺ ሚሊሻዎቹን ቀደም ሲል ሶሪያ ዉስጥ ማስፈሩ ይታወቃል። የሊዋ አልፋጢሚዩን ብርጌድ በኢራቅና በኢራን ጦርነት ወቅት ከኢራን ጋር አብሮ የተዋጋ ሲሆን ሶሪያ ዉስጥ በትጋት እንደሚምቀሳቀስም ይታወቃል። 
የዙል ፈቅር ሚሊሻዎች
እራሳቸዉን ዙል ፈቅር የሚል መጠሪያ የሰጡትና በግል የተደራጁት የኢራቅ ሺዓዎች ሶሪያ ዉስጥ ሱኒዎችን ለመዋጋት ሰፍረዋል። ከአቡ ፋድል አል አባስ ብርጌድ ጋር በመተባበር ሰይዳ ዘይነብ በመባል በሚታወቀዉ አካባቢ ሰፍረዋል።
የኢራቁ በድር ማህበር፡
የኢራቁን የቀድሞ ፕሬዝዳንት በመቃወም የተቋመዉ ሺዓዉ የኢራቁ በድር ማህበር ሁለት ሺ የሚደርሱ ሚሊሻዎቹን ወደ ሶርያ ልኳል።የሶርያ ሱኒዎችንም እየተዋጋ ነዉ።
ከፊል ዘይነብ፡
በኢራቁ ሙቅተዳ አልሳደር ከሚመራዉ የመህዲ ጦር የተገነጠለዉ ከፊል ዘይነብ የሰኘዉ ጦርም ሶርያ ዉስጥ ሰፍሯል።አቅሙ በቻለዉ መጠንም የሶር ያን የበሻር አል አሳድ መንግስት ይደግፋል። የአዋቱን የሶር ያ መንግስት ለመደገፍ ሐሉን ይዞ ሶር ያ ዉስጥ ከትሟል።
አል ሰይብ አልሐቅ 
ከኢራቁ የመህዲ ጦር የተገነጠለዉ አል ሰይብ አል ሐቅ በኢራን የሚደገፍ ነዉ። ከሒዝቡላህ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለዉ ይታወቃል። ነዉጠኛ፣አሽባሪ፣የማህበራዊ ግልጋሎት ሰጭ፣የፖለቲካ ሐይል እንደሆነ የሚታወቀዉ አልሰይብ አል ሐቅ በጣም አደገኛ የሆነ የሺአ ሐይል መሆኑ በመዛግብት ላይ ሰፍሯል።አደገኛነቱን በተግባር ለማሳየት ሶር ያ ዉስጥ ይገኛል።
*****
መሰረቱን ኢራን ዉስጥ አድርጎ በመካከለኛዉ ምስራቅ ዉስጥ የሚቀሳቀሰዉ የሺዓ አብዮታዊ ጥምር ሐይል በኢራቅ፣በባህሬን፣በየመን፣በሊባኖስ፣ በሶርያና በአፍጋኒስታን ዉስጥ የሚያደርገዉ ወታደራዊ መስፋፋት በምእራቡም ይሁን በምስራቁ አለም ባሉ የመገናኛ ብዙሗን እምብዛም አትኩሮትን አላገኘም። 
ይህንን ቀዉስ ሱኒ ሙስሊሞች የሺዓና የሱኒ ክፍፍል እንዳይመስል እራሳቸዉን በፖለቲካዊ ተዓርሞ ዉስጥ አስገብተዉ ከእዉነታዉ ይሸሻሉ የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፤ የሺዓ የጦር ሐይሎች ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ ጦርነት ላይ መሆናቸዉን ግን አይክዱም። የሺዓ ቡድናዊ ሚሊሻዎችና መንግስታዊ መዋቅር ያላቸዉ የጦር ሐይሎቻቸዉ በአመራር የተለያዩ ቢመስሉም የአላማ መስተጻምር ያላቸዉና ግባቸዉ አንድ መሆኑን የመካከለኛዉ ምስራቅ የፖለቲካ ሒደትን የሚያጠኑ አካላቶች ይገልጻሉ።
ሶሪያ ዉስጥ ጥምር የሺዓ ሐይል ሱኒዎችን እየተዋጋ ነዉ የሚሉት ተንታኞች፤ የየመኖቹ የሺዓ የሁቲ አማጽያን መካን ወይም ጅዳን ኢላማ ያደረገ ሚሳኤል ተኩሰዉ በሳኡዲ ጸረ-ሚሳኤል ተመቶ መውደቁን እያስታወሱ፤ የመገናኛ ብዙሗን ቸልታንና የመንግስታትን ዝምታን በመገምገም ወደፊት ሊከሰት የሚችለዉን አሻግረዉ በማየት ስጋታቸዉን ያስረዳሉ።

No comments:

Post a Comment