Monday, November 28, 2016

በወያኔና በቻይና መካከል ጠብቅ ያለ ለወታደራዊ ስምምነት ተደረሰ


በወያኔና በቻይና መካከል ጠብቅ ያለ ለወታደራዊ ስምምነት ተደረሰ
የወያኔና የቻይና ጋብቻ ወደ ወታደራዊ ስምምነት መድረሱ ታወቀ፡፡ በተደጋጋሚ ከቻይናና ከወያኔ የሚሰሙት ቻይና በፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ እንደማትገባ ቢሆንም በተለያዩ አጋጣሚዎች በተጨባጭ እየታየ ያለው ግን ቻይና ወያኔን በአምባገነኑ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አምሳል እየቀረጸችው እንደሆነ ነው፡፡
ቻይና በአጭር ሞገድ የሚተላለፉ እንደ ፍኖተ-ዴሞክራሲንና መሰል ሬድዮኖችን በማፈን በቀጥታ ስትስታፍ፣ በማፈን ምህንድስና ትምህርት የወያኔን ደህንነቶች አሰልጥናለች፡፡ ቻይና የኢንተርኔት ሰበራንና የተንቀሳቃሽ ስልኮችን ጠለፋ በማካሄድ በሶሻል ሚዲያ ሕዝቡ የሚቀባበለውን መረጃ እንዳያገኝ እያደረገችም ነው፡፡
በቅርቡ ከወጡ ይፋ መግለጫዎችም ሆነ ከመከላከያ አካባቢ ሾልኮ ከወጣው መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው ቻይናና ወያኔ በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች ጥብቅ ትብብር ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በስምምነቱ መሰረት ቻይና በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኦጋዴን ውስጥ መገኘቱ ከተነገረለት ጋዝ ጋር በማያያዝ በጅቡቲና በድሬደዋ መሀል አንድ የጦር ሰፈር ትመሰርታለች ተብሏል ፡፡ ይህ ሁኔታ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ያለውን የቻይናን የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ እውን ያደርገዋል የሚሉ በርካቶች መሆናቸውን ተገንዝበናል፡፡ Finote Democracy

No comments:

Post a Comment