Friday, November 18, 2016

ልትሸፍቱ ትችላላሁ በሚል ስጋት ዐማሮች በገፍ እየታሰሩ ነው፤


ልትሸፍቱ ትችላላሁ በሚል ስጋት ዐማሮች በገፍ እየታሰሩ ነው፤ Muluken Tesfaw
የወያኔ አገዛዝ ዐማሮችን በገፍ ማሰሩ እንደገና አገርሽቶበታል። በሁሉም አካባቢዎች ዐማሮች እየተለቀሙ እየታሰሩ ቢሆንም በወልቃይትና በአርማጭሆ የተባባሰ መሄዱን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ዛሬ ኅዳር 9 ቀን 2009 ዓም የእነ አቶ አታላይ ዛፌ የቅርብ ጓደኛና የወልቃይት ተወላጅ የሆኑት አቶ ገብረመስቀል ማመይ በብአዴን ልዩ ኃይሎች ረፋድ ላይ ተይዘው ተወስደዋል። ትናንት እነ አቶ ዘውዱ ነጋን ጨምሮ በከተማ በቤታቸው የነበሩ በርካታ ዐማሮች ልትሸፍቱ ትችላላችሁ በሚል ምክንያት ተይዘዋል።
በኹመራ ወንዝ ውኃ ሲጠጡ የነበሩ 5 ያክል ወጣቶችም በአንድ ባንዳ የአካባቢው ተወላጅ ጥቆማ መያዛቸውን ለማወቅ ችለናል።
በተያያዘም በደብረ ታቦር፣ በወገራ፣ በለሳ፣ ጎንቻ ሲሦ እነሴ፣ እነሴ ሳር ምድርና እናርጅ እናውጋ አካባቢዎች ብዙ ወጣቶች መታሰራቸውን ሰምተናል። በደብረ ታቦር አቶ ወርቁ ዓለም የተባለ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ወጣቶችን በማስያዝ የለየለት የባንዳነት ሥራ እያከናወነ እንደሆነ ሰምተናል። አቶ ወርቁን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች እያጠናቀርን ሲሆን ማጣራቱ እንዳለቀ ከፎቶ ግራፍ ጋር እናቀርባለን።
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!

No comments:

Post a Comment