Thursday, November 24, 2016

የንፁሃንን ደም የፕሮፖጋንዳ ማሽን ማድረግ ይቁም ! ይህ የታጋዩ ሬሳ እንደሆነ ተነግሮናል ።



ኄኖክ የሺጥላ



ይህ የታጋዩ ሬሳ እንደሆነ ተነግሮናል ። የሰውነቱ ማበጥ ቢያንስ ከሞተ ሶስት ቀን የቆየ ሰው ሊሆን እንደሚችል ፎቶውን Analyze ያደረጉ የህክምና ባለሙያዎች ገልጠውልኛል። የሰውነቱ ማበጥ በደንብ ይታያል። ደረቱ በጥቁር ጨርቅ የተሸፈነው ደረቱን በጥይት ብሎ ነው የሞተው የሚል ድባብ ለመፍጠር ነው ። ይህም In any forensic study there isn’t a single case where a suicide is happened by gunning down oneself on the chest ! ራሱን የሚገል ሰው በምንም አይነት ጥይት ደረቱ ላይ ተኩሶ አይሞትም !

ደረቱን እንኳ መትቶ ሞተ ቢባል ፥ ይህ ሰው የወደቀበት አካባቢ ደም አይታይም? ደረቱ ላይ የተመታ ሰው ደሙ በቀላሉ የሚቆምም አይደለም። ደረታችን ላይ እጅግ በጣም ብዙ የደም ስሮች አሉ።

በተጨማሪ ይህ በትክክል ለፎቶ ተስተካክሎ የተነሳ ሬሳ ስለመሆኑ እጆቹን ፥ ጭንቅላቱ ያረፈበተን ቦታ እና የእግሮቹን ሁኔታ ማየት ይቻላል።

1) ይህንን ፎቶ የለቀቀው ወያኔ ነውን ? አይ እኛ ነን ካላችሁ ልብሱን አውልቆ ነው እራሱን ያጠፋው ?
2) ከሆነስ ፎቶውን በሚነሳበት ጊዜ መሳሪያው የት ገባ? በምን አይነት መሳሪያ ነው ይህ ሰው ራሱን ያጠፋው ?
3) ወይስ ጓደኞቹ ታስረው የሞቱበት የሻዕቢያ 5 ሜትር የማሰቃያ ጉድጓድ ውስጥ ነው ይህ ሰው የሞተው ?

በተጨማሪም ፎቶውን ያነሱት የትግል አጋሮቹ ከሆኑ ፥ ወዳጃቸውን እርቃኑን ለማንሳት ለምን ፈለጉ ? በትግል ውስጥ የመጀመሪያው ነገር የታገዩን በደን መከፈን ( ወይም መሸፈን ) ነው ።

ሌሎች መረጃዎቹን ወዳጆቻችን በዝርዝር እየሰሩበት ነው ። ስልክ ደውለው በተባለው ቦታ በተባለው ቀን ውጊያ እንዳልነበረ የደረሳቸው መረጃ ያስረዳል ። ተመሳሳይ የድምፅ መረጃዎች በቅርብ ለህዝብ ይፋ ይወጣሉ! የንፁሃንን ደም የፕሮፖጋንዳ ማሽን ማድረግ ይቁም ! ይህ ፍፁም አሪዮሳዊነት ነው!

ኄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment