ብአዴን በሐረር ቤተ መንግሥት የጠራው ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፤ Muluket Tesfaw
ብአዴን 36ኛ ዓመቱን ለማክበር በዓለማያ ዩንቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎችንና በሐረር ከተማ ይደግፉኛል ያላቸውን ነዋሪዎች ሰብስቦ ለማነጋገር ኅዳር 9 እና 10 ቀን 2009 ዓም ሙከራ አድርጎ ነበር። ከዓለማያ ዩንቨርሲቲ ዋና እና ሐረር ግቢዎች ተማሪዎችን ወደ ቤተ መንግሥት አዳራሽ የሚወስዱ ዐሥር አውቶቢሶችን ዩንቨርሲቲው መድቦ ነበር።
የዐማራ ተማሪዎች “እናንተ እነማን ናችሁ የምትሰበስቡን? ለዐማራ ሕዝብ ሳትቆሙ የ36 ዓመት ጎልማሳ ነን ትላላችሁ? ለመሆኑ በሕወሓት የሚገደሉ ወንድሞቻችን ሳትታደጉ እንዴት እኛን ለማየት ደፈራችሁ?” በማለት ተወካዮችን አሳፍረው መልሰዋል።
ከዩንቨርሲቲው መረጃውን ያደረሱን ተማሪዎች እንደሚሉት በስብሰባው የሕወሓትና የኦሕዴድ ተወካዮች ተገኝተው ለማገዝ ቢጥሩም የዐማራ ተማሪዎች ስብሰባውን ለራሳቸው ምክክር በመጠቀም የብአዴንና የሕወሓት ተወካዮችን አባረዋል። የዐማራ ተማሪዎች ከፍተኛ ውክቢያ እና እንግልት ቢደርስብንም ከሕዝባችን ጎን መቆማችን እንቀጥላለን ሲሉ አሳስበዋል።

የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!
No comments:
Post a Comment