የወያኔ የሹመት አጀንዳ = የሳምንቱ ምርጥ ቀልድ = ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ አይንአውጣነት – ከጅምሩ ኋላፊነት የጎደለው አገዛዝ ስለ ተጠያቂነት ሞራሉ የለውም። በኢትዮጵያ ስር የሰደደውና የተንሰራፋው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሙስና እና የመልካም አስተዳደር ችግር ሁሉ ያሳተፈ ስል ነቀል ለውጥ እስካልተደረገ ድረስ በዘራፊው ሕወሓት መራሽ አገዛዝ ይስተካከላል ማለት ዘበት ነው። ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ አይን አውጣነት ሽወዳ ይቁም ፤ የወያኔ ሹመት አጀንዳው ተከትሎ ሃይለኛ ወቀጣ እየተደረገ ነው። ወያኔን ለማያውቅሽ ታጠኙ በሏት። ሕዝባዊ ንቅናቄ የፖለቲካና ኢኮኖሚ በድርቅ እና በተለያዩ ጫናዎች አጣብቂኝ ውስጥ ከውስጥ እና ከውጪ ስትገባ ሕወሓት ሽወዳ ለማድረግ የምትጠቀምበት ዘዴ አንዱ ማኮላሻ አጀንዳዎችን በመፍጠር ከጀርባ ሴራዎች ላይ ማጠንጠን ነው። በሕወሓት ኣጨብጫቢዎችና በተቃዋሚው ጎራ ድጋፍና ትችትን ያስከተለው የሃይለማርያም የወጥ ቤት ካቢኔት የሕዝቦች ነጻነት ባልተረጋገጠበት ሃገር ምን አይነት ፌዝ ነው የተያዘው፧የሳምንቱ ምርጥ ቀልድ ነው የሆነብኝ።በሃገሪቱ ሁለት የሚታይና የማይታይ መንግስቶች ኣሉ የሚታየው በሃሰት ተተብትቦ ሲኖር የማይታየው ግን ይገላል ያስራል ያሳዳዳል፤
የወያኔ ባለስልጣናት ተሰብስበው ችግሩ እኛ ጋር ነው አሉ እየተባልን ያለነው ሽተታቸውን አመኑ ብለን ሆዳችንን ለማባባት ከሆነ ሞኛቸውን ይፈልጉ፥፥ካሁን ቀደም ከጠ/ሚ ተብዬ ቢሮ ጀምሮ በተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያቤቶች እና አካሎቻቸይ ያልተባል ያልተማል ያልተነገር ነገር የለም ያልተሰበሰበ ያልተገመገመ ያልተወሰነ ወዘተ የለም፥ሆኖም ነገሮች ሁሉ ማዘናጊያ ከጊዜ አጣብቂኝ ለመውጣት የሚጠቀሙባት ልማታዊ ሽወዳ ናት፥በዘረፋ እና በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ላይ የተሰማራው ወያኔ ጭፍሮቹን እያስጨበጨበ አዲስ የግፍ ስልት ለመቀየስ ብቅ ማለቱን ያመለክታል፥፥ላለፉት 25 አመታት የት ነበረኡ ? ይህ ሁሉ የወያኔ ባለስልጣን ዛሬ ስለ ሃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚነግሩን?ሞራላቸውስ ? ለመሆኑ ብሄራቸውን እና አብሮ አደግነታቸውን መከታ በማድረግ በየመንግስት መስሪያ ቤቱ የተሰገሰጉት እነማን ናቸው? የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በየሃገሩ የሚገኙ ኤምባሲዎች በዋቢነት ማስቀመጥ ይቻላል::ይህ ተባለ ያ ተባል ብሎ ስለ ቆራጥነት ከማላዘን መጀመሪያ እርምጃው ከሕወሓት ተጀምሮ ተግባራዊ ስራዎች ሲተገበሩ ነው ቆራጥነት የሚባለው፥እውነት ከሆነ ላላዛኞቹ ብቻ፥፥
የወያኔ ባለስልጣናት በተለይ ሕወሓት በዘረፋ እና በብሄር ተኮር መጠቃቀም ግንባር ቀደም ባለኔትዎርክ ነው ቀሪ የወያኔ ድርጅቶችም በኔትወርክ ቢደራጁም ከሕወሓት እውቅና ውጪ አይንቀሳቀሱም የሁሉ እኩይ ተግባር መሪ ሕወሓት ነው!! ካሁን ቀደም በተለያየ ጊዜ የሙስና ኔትወርኮችን ለመበጣጠስ ተጠያቂነት እና ሃላፊነትን ለማስፈን የተደረገው ሙከራ በሌቦች ባለስልጣት ከሽፎ የመልካምነትን ጥያቄ ያነገቡ እስር ቤት ታጉረዋል :: ለዚህም ዋና ተጠቃሽ በሙስና እስር ቤት የሚገኘው መላኩ የሕወሓት ስውር እጆች አላሰራ አሉን ስላለ ብቻ ተይዞ ወደ ወህኒ ተወርውሯል::አሁን ከመላኩ እና ከገብረዋህድ በላይ ሃገሪቷን ያራቆቱ ቡድኖች ጠፍተው ነው? ይህ ደግሞ በብሄር በመንደር በአብሮ አደግነት የተሳሰረው ኔትወርክ በከፍተኛ ባለስልጣት እጅ(በሕወሓቶች) እንደሆነ በገሃድ ያሳያል::
በኦሮሚያና በኣማራ ክልል የተደረጉ ግድያዎች መብትና ነጻነትን የጠየቁ ሕዝቦችን በጥይት መፍጀት ማሰር ማሳደድ ከኣገዛዙ ኣከፊ ተግባራቶች ግንባር ቀደም ናቸው። በሃገሪቱ ሁልት የሚታይና የማይታይ መንግስቶች ኣሉ የሚታየው በሃሰት ተተብትቦ ሲኖር የማይታየው ግን ይገላል ያስራል ያሳዳዳል!የሰው ልጆች ነጸነት ባልተረጋገጠበት ዜጎች በአሸባሪ ታርጋ እስር ቤት በሚገቡበት አገር እንዴት መልካም አስተዳደር ይረጋገጣል?መጀመሪያ ነጻነት!!! ከአጣብቂኝ ለመውጣት የተደረገ የልማታዊ ሽወዳ የፖለቲካ ስልት አንዲት ቅርንጫፍ ነው::ይህ ጉዳይ ቆራጥ እርምጃ ከተወሰደበት የሕወሓት እና ጭፍሮቹ ጉሮሮ መቁረጥ ስለሆነ መተግበር ያስቸግራል አሊያም ይህን ለመተግበር ከተቃዋሚዎች ጫን ያለ የትግል ስልት ይዞ መዝለቅን ይጠብቃል::ላለፉት 25 አመታት ሃላፊነት በጎደለው መንገድ በዘረፋ እና በሃሰት ፕሮፓጋንዳ አገር እመራለሁ የሚል ቡድን በየትኛው ሞራሉ ሰላማዊ መንገድን በአንድ ጀንበር ይቀበላል::ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ ልማታዊ ሽወዳ ይቁም::ከጅምሩ ኋላፊነት የጎደለው አገዛዝ ስለተጠያቂነት ሞራሉ የለውም!!!
No comments:
Post a Comment