Wednesday, November 2, 2016

የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ኣሻንጉሊት ሲሆን ወሳኙ ኣካል ሕወሓት/ወያኔ እንደሆነ ይቀጥላል። የዶክተሮች ጋጋታ ከዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ጋር ፉክክር ኣድርጎታል።


 የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ኣሻንጉሊት ሲሆን ወሳኙ ኣካል ሕወሓት/ወያኔ እንደሆነ ይቀጥላል። የዶክተሮች ጋጋታ ከዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ጋር ፉክክር ኣድርጎታል። 
Image may contain: one or more people and text
 በኢሕአዲግ ኣገዛዝ የሕወሓት የበላይነት የሚቆመው ሕወሓት ስልጣኑን ለሕዝብ ሲያስረክብ ብቻ ብቻ ነው፤ ኣሻንጉሊቶች መሰብሰብ የለመደው ሕወሓት የፓርቲና የመንግስት ስራ ቀላቅሎ ሕዝብን ሰላምና ፍትህን ኣሳጥቶ በመግደል በማሰር ላይ ይገኛል። ሃገራችን በወታደራዊ ኣገዛዝ በኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ስር ባለችበት በዚህ ወቅት ላይ ሲቪል ሚኒስትሮችን ያዉም ታማኝ ባሪያዎችን መሾም ማጭበርበር ነው።። በፖለቲካ ማጭበርበር ደሞ ወያኔ የተካነበት ስራው ነው። ሃሰትን ማራባት ኣራብቶ ማሰራጨት የወያኔ ስራው ነው።
ወያኔ የምሁራን ስብስብ እንዲባል ዶክተር ፕሮፌሰር እያለ ሚኒስቴር መሾሙ ሳቅ ለመፍጠር ካልሆነ በስተቀር ለሕዝብ የሚፈይደው ኣንድም ነገር የለም። ዲያሶፖራ ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር ዶክተር ፕሮፌሰር እያሉ ከመሾም ይልቅ ለሕዝብ ጥያቄ መመለስ በጣም ቀላል ነው። ይህ ግን ወያኔ ለማድረግ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ሕዝብን በማታለል መቀጠሉን ለማሳየት ታዛዥ የሆኑ ከብቶች በሚኒስትርነት ሾሟል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ያውም ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ። የሚኒስትሮን መለዋወጥ ከጉልቻ መለዋወጥ ኣይለይም ኣንዳጁ ኣካል ስልጣል ሲለቅ ነው የሚነደው ኣካል እፎይ የሚለው እሳቱ ስልጣን ሲለው የኣምባገነኖች ነበልባል ስልጣን ሲለቅ በእሳት የሚለበለበው ሕዝብ ሰላም ያገኛል። ተሿሚ ሚኒስትሮች ራሳቸውን በምቾት በማኖር ለሆዳቸው ከማደር ውጪ በሃገር የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ምን ኣይነት ለውጥ ኣያመጡም።ይህ ለይስሙላ የሚደረግ ተግባር የሕዝብን ትግል ኣያቆምም። ትግሉ ይቀጥላል።

No comments:

Post a Comment