Wednesday, November 23, 2016

ጫናው መበርታቱን ተከትሎ በደሕንነት ቢሮው የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን በማንሳት ዙሪያ የሚነጋገር ስብሰባ ተደረገ።



 ጫናው መበርታቱን ተከትሎ በደሕንነት ቢሮው የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን በማንሳት ዙሪያ የሚነጋገር ስብሰባ ተደረገ። በሳሞራ የኑስ እና በጌታቸው አሰፋ መካከል አለመግባባት አለ የሚለው ሕወሓት የምትንዛው አሉባልታ እንደተጠበቀ ሆኖ የሕወሓት አመራሮች ብቻ የተሳተፉበት ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን በማንሳት ዙሪያ በአትኩሮት የተወያየበት የምእራባውያንን ጫና በተመለከተ መሆኑ ታውቋል።
በዚህ ስብሰባ ላይ ሲራጅ ፈርጌሳ የተባለው ሰውዬ ጨምሮ የኮማንድ ፖስቱ አመራሮች አለመሳተፋችውንና ስብሰባው በትግሪኛ መደረጉን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል። በሳሞራና በጌታቸው መካከል ያለው ሽኩቻ የስልጣን ሳይሆን የተሰሚነት ነው የሚሉ ጉዳዩን የሚከታተሉ ኣካላት ይህን ያህል የሚጋነን ችግር በሕወሓት ውስጥ እንዳሌለ ሲናገሩ ይልቅ መከፋፍል እና የሚጋነን ችግር ያለው በለውጥ ሃይሉ ውስጥ ነው በማለት ጠቁመዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና የራሳቸውን ያላወቁ የብአዴን ኣባላት የኦሕዴድ ካድሬዎችን በሕወሓት ሰላይነትና በሕዝብ አስፈጅነት እየወነጀሉ ነው።ከአማራ ክልል ምክር ቤት አከባቢ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የራሳቸውን ያላወቁ የብአዴን አባላት የኦሕዴድ ካድሬዎች የሕወሓት ተላላኪዎች በመሆን እየበጠበጡን ነው ሲሉ በመወንጀል ላይ ሲሆኑ የኦሕዴድ ሰዎች ዝምታን መምረጣቸው ታውቋል። 

No comments:

Post a Comment