ፌስቡክ በሩብ አመት 2.4 ቢ. ዶላር አትርፏል የተጠቃሚዎቹ ቁጥር 1.79 ቢ. ደርሷል
ታዋቂው የማህበራዊ ድረገጽ ፌስቡክ ባለፈው መስከረም በተጠናቀቀው የዘንድሮው ሶስተኛ ሩብ አመት 2.4 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉንና 7.01 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ባለፈው ሳምንት አስታወቀ፡፡
ፌስቡክ የሩብ አመት ትርፉ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ166 በመቶ እድገት በማሳየት 2.4 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን እንዳስታወቀ የዘገበው ስካይ ኒውስ፤ትርፋማ እንዲሆን ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ያበረከተው ከሞባይል አገልግሎት ማስታወቂያ ያገኘው ገቢ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር 1.79 ቢሊዮን መድረሱን ያስታወቀው ኩባንያው፤ በሞባይል ብቻ ፌስቡክ የሚጠቀሙ ደምበኞቹ ቁጥርም 1.66 ሚሊዮን መድረሱን አመልክቷል፡፡
ኩባንያው በቀጣዩ አመት ኢንቨስትመንቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያስፋፋ ማስታወቁንዘገባው ጠቅሶ፣ ከእነዚህ ኢንቨስትመንቶች መካከልም በድሮኖች አማካይነት ለገጠር አካባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ማዳረስ አንዱ እንደሆነ
No comments:
Post a Comment