Thursday, November 24, 2016

ዜናው ግልፅ አይደለም ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ(ገብርዬ)ራሱን ለማጥፋቱ ምንም ማስረጃ የለም። የሻእቢያ ስለባ ነው የሚሉ በርክተዋል። ( ቆንጂት ስጦታው)

maj-mesafint-tigabu

ዜናው ግልፅ አይደለም ነው ያልነው ። እወቁ ካላችሁ በደንብ እንወቅ ! የተነገረንን ሁሉ አንቀበልም ! የተባለው ሁሉ ውሸት ነውም አንልም ! የመመርመር መብት ግን አለን !
ዜናው ግልፅ አይደለም ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ(ገብርዬ)ራሱን ለማጥፋቱ ምንም ማስረጃ የለም። የሻእቢያ ስለባ ነው የሚሉ በርክተዋል። ( ቆንጂት ስጦታው)
በሰሜን ኢትዮጵያ ድንበር ኣከባቢ በተነሳ ግጭት የበላይነቱን ይዣለሁ የሚለው የግንቦት ሰባት ድርጅት የጦር መሪዬ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ(ገብርዬ) በወያኔ ጦር ተከቦ እጄን ኣልሰጥም በማለት ራሱን ኣጠፋ ሲል የለቀቀው ዜና ብዙ የሚጣረሱና የሚጋጩ ዘገባዎችን በመያዙ ሻለቃው ራሱን ለማጥፋቱ ምንም ማረጋገጫ ኣለመገኘቱንና ምናልባትም በኣቋማቸው ምክንያት የሻእቢያ ስለባ ከሆኑ ታጋዮች ኣንዱ ነው ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ።
ሻለቃ መሳፍንት ከዘመነ ካሴ ጋር በመሆን በግንቦት ሰባት ላይ ከፍተኛ ትችት ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ለጦርነት የሚሆን በቂ ዝግጅት ኣድርገናል ለምን አንንቀሳቀስም በሚል በተዴጋጋሚ ከኮሎኔል ፍጹምና ከሌሎች የሻእብያ ኣካላት ጋር ይጋጭ እንደነበር በኣስመራ የኣርበኞች ግንባር ኣባላት ይናገራሉ። ሻለቃ መሳፍንት ወደ ጦር ሜዳ ተንቀሳቀስ ተብሎ ሲላክ ኣብረዉት በቡድን የተላኩ ጥቂት ሰዎች ከደምህት ተመልምለው የተወሰዱ እንደነበር የኣይን እማኞች ይናገራሉ። ሞተ ተብሎ የተነገረውም ወዲያው ሲሆን የሟቹ ኣስከሬን ግን በማን ቭድዮ እንደተነሳ ፎቶው እንዴት ተደርጎ እንደተገኘ ማብራሪያ ኣልተሰጠም።ይህ ብቻ ሳይሆን ሻለቃው ራሱን ለመግደሉ የሚያረጋግጡ ምልክቶች በሰውነቱ ላይ የለም ወያኔ ከባው ራሱን ካጠፋ ወያኔ ቦታውን ለቃ ሬሳውን ትታ እንዴት ልት ሄድ ቻለች የተገደለበት ቦታስ ድረስ የሻእቢያ ሚዲያዎች እንዴት ሊደርሱ ቻሉ የሚሉ ጥያቄዎች በተከታታይ እየተነሱ ይገኛሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የግንቦት ሰባት ካድሬዎች ሻለቃውን የኛ ጀግና በማለት የኣርበኞች ግንባር ሰዎች የጦር ሜዳ ውሎ እንዳሌላቸው በመናገር ላይ መሆናቸውን የኣርበኞች ግንባር ኣባላትን እያስቆጣ ይገኛል። ይህ የሚያሳየው በኣርበኞች ግንባርና በግንቦት ሰባት መካከል ያለው ገመድ የሃሰት መሆኑን ነው ሲሉ ኣስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ግንቦት ሰባትን እርቃኑን ያወጣው ሄኖክ የሺጥላ እንደሚከተው ጽፏል።
እነ ኮነሬል ፍፁም ሁለት ጓደኞቼን ከገደሉ በኋላ ፥ በወያኔ እጅ ላለመውደቅ ራሳቸው ገደሉ ነበር ያሉን። መሳይ መኮንን ኤርትራ በወረደ ጊዜ ፥ ከአውሮፓ የገቡትን ታጋዮች ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸው ነበር ። የነዚያ ልጆች ቃለ መጠይቅ በኮረም ነዋሪ የሆነችው ብርቱካን አሊ ልጇን በራብ ቀብራ ፥ አይ ታሞ ነው የሞተው ብላ ለሁለተኛ ጊዜ በወያኔ ከተቀረፀችው ጋ የሚያመሳስሏቸውን ብዙ ነገሮችን አስተውዬበታለሁ።
ጥያቄ
በወያኔ እጅ ላለመውደቅ ራሱን ሲያጠፋ ፥ በወያኔ ተከቧል ማለት ነው አይደል ? በጥይት ተመቶ ቆስሎ ነበር ?
እሱ ራሱን ባጠፋበት ሰዓት ፥ እሱ ራሱን ሲያጠፋ ያየ ግን ደሞ በወያኔ ያልተያዘ አካል አለ ማለት ነው ? አሁንም ማወቅ እንፈልጋለን ! ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ ሻዕቢያ በአቋማቸው ምክንያት የገደላቸውን ሰዎች መርዶ የምናስተላልፍበት አጋጣሚ ስላለመሆኑ አሁንም ህዝቡ ማወቅ ይፈልጋል ። ይህንን የምለው በተከታታይ ጓደኞቼን ሻዕቢያ እንዴት አድርጎ እንዳጠፋቸው ስለማውቅ ነው !!!! ስለ ሚሽን 1725 በቅርቡ በስፋት ዕፅፋለሁ ። በዚህ ሚሽን እነ ኮነሬል ፍፁም የአማራ ልጆችን ጭልጋ ላይ እንዴት አስከብበው በወያኔ እንዳስደበደቧቸው ለህዝብ የማሳውቅበት ነው።
ዜናው ግልፅ አይደለም ነው ያልነው ። እወቁ ካላችሁ በደንብ እንወቅ ! የተነገረንን ሁሉ አንቀበልም ! የተባለው ሁሉ ውሸት ነውም አንልም ! የመመርመር መብት ግን አለን ! የዚህ ልጅ ቤተሰቦች የልጃቸውን ሞት ( እውነተኛ አሟሟት ) የማወቅ መብት አላቸው። ከዜናው አንፃር ገለፃው ብዥታ አለበት። ይብራራ ነው ያልነው!!! አዎ ይብራራልን የሞተው አማራ ነውና!!!!

No comments:

Post a Comment