Saturday, November 19, 2016

ሰከን ብለን መፍትሄ እናስብ።ግለሰባዊና ድርጅታዊ ግብረገብነት መጥፋት ለወያኔ ክፍተት ፈጥሯል።= ልብ ያለው ልብ ብሎ ያንብብ።


Image may contain: text
ሰከን ብለን መፍትሄ እናስብ።ግለሰባዊና ድርጅታዊ ግብረገብነት መጥፋት ለወያኔ ክፍተት ፈጥሯል።= ልብ ያለው ልብ ብሎ ያንብብ።
የኢትዮጵያውያኑ መገናኛ የሆነው ማህበራዊ ድረገጽ የስድብ ቀጠና ሆኗል። ከመፍትሄ ሃሳብ ይልቅ ከሚያቀራርቡ ኣንደበቶችና ብእሮች ይልቅ ትችትና ስድብ ኣውቅልሃለሁ ኣታውቅልኝም የሚለው ዲያስፖራው ክፍል ሃያ ኣራት ሰኣት ሲጠዛጠዝ ሃገር ቤት ያለው ሕዝብ ግን ትግሉን ቀጥሎታል። ሃሳባችንን ኣቀራርበን ለሃገራችን መላ እንዘይድ ከሚለው ይልቅ ሃሳቡን በነጻነት የሚገልጸውን ማሸማቀቅ ቀጥሏል።ጎን ለጎንም በሃሳብ መግለጽ ሰበብ የድርጅቶችንና የግለሰቦችን መብት የሚጋፉና የግል ጉዳይን የሚተበትቡ ዘምተዋል።ለዚህና መሰል ጉዳዮች ኣስፈላጊ የሆነው ጉዳይ ቢኖር ተደማምጦ መላ መፈለግና ተከባብሮ ትግልን መቀጠሉ ያዋጣል።ተቀራርቦ መነጋገር መፍትሄ ነው የለውጥ ሃይሉን በኣንድ ጥላ ስር ማሰባሰብ መፍትሄ ነው። መመካከር = መደማመጥ = መከባበር = ሃሳቦችን ሰብስቦ የዳበረ ሃሳብ መፍጠርም መፍትሄ ነው።
በማህበራዊ ድህረገጽ ብዙ ኣመታትን ኣሳልፈናል፤በበሰሉ ወገኖች ስልከበርበት ባልበሰሉና በስሜታውያን ዛሬም ባልተሻሻሉ ወገኖች ተዋርደንበታል፤ ይህን ሁሉ ኣሳልፈን ኣቻችልን ሁላችንም ለዚህ ደርሰናል። ከባለፈው ሂደቶች ተምረን የበሰልን እንዳለን ሆነን ያልበሰሉና የባሰባቸው ድርጅታዊና ግለሰባዊ ስነስርዓት ያልፈጠረባቸው ኣሁንም እየተልፈሰፈሱም ቢሆን መሞጣሞጣቸውን ኣላቆሙም። እያልን ያለነው ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ነው ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ካልን ደግሞ በጋራ መታገል በጋራ ማደራጀት በጋራ ማጥቃትና በጋራ መቆም ችላ የማይባል ሃገራዊ የኣንድነተ ኣጀንዳ ሊሆን ይገባል።
የፍረጃ የትንኮሳ የግፊያ የቅፈላ የማግለልና ተመሳሳይ የፖለቲካ ጡዘቶች የግድ ሊቆሙና ሁሉም በጋራ ሊሰባሰቡ ይገባል። ካልደፈረስ ኣይጠራምን ከመከተል ይልቅ ተረጋግቶ ሰከን ማለትን ኣውቀን ለመፍትሄው መንገድ ማበጀት ኣለብን።ጸረ ወያኔ ኣቋም ይዞ የሚታገለው ሁሉ ነጻ ኣውጪ ነው በተለያዩ ብሄሮች ስም ይሁም በኣንድ ኢትዮጵያ ስም የሚታገለው ሁሉ ኣላማውን እንደያዘ ሕዝቦችን ነጻ ሊያወጣ የሚችል ማኒፌስቶ ስር ሊሰባሰብ ይገባል።
የኣንድ ሰሞን የሆያሆዬ ፖለቲካ ሊቆም ይገባል። በትውውቅና በመንደርተኝነት የሚጓዝ ፖለቲካ ሊቆም ይገባል።ከስድብ ይልቅ ሃሳብ በሃሳብ ኣሸንፎ የሃሳብ የበላይነትን የያዘ መስመር ማበጀት ይፈለጋል።ሁሉን ኢትዮጵያውያን ባሳተፈ መልኩ የሚደረግ ተግባር መፍትሄውን ያመጣዋል። የተለየ ሃሳብ ያለውን ሁሉ ወያኔ ብሎ በመፈረጅና ካለመብሰል በስሜታዊነት የሚያጨበጭበውን የኔ ነው ከማለት ራሳችንን ልንታዴግ ይገባል። ግለሰቦች ራሳቸውን ስነስርዓት ኣስተምረው ሊመሩት ይገባል። ድርጅቶችን ኣባሎቻቸውን ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ኣስተምረው በሃሳብ የበላይነት እንዲያምኑና የማይመቻቸውን ሃሳብን በዳበረ ሃሳብ እንዲያፈርሱ እንዲታገሉ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ኣብረው ባሳለፉት ጊዜአያት የነበረውን ሂደት ኣለመስማማቶች ሲፈጠሩ ማውራት እንዲሁም የተሻለ ነጻ ሃሳብ ይዞ የመጣውን ማሽማቀቅ በፍጹም ስኬትን ኣይፈጥርም።ጥላቻን እያሰፋ ለጠላት ክፍተት የሚሰጥ ስራዎችን መስራት ልናቆም ይገባል።

No comments:

Post a Comment