Tuesday, November 8, 2016

” ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር” የሚል መሪ ሐሳብ በመያዝ የአማራ ማህበረሰብ መሐበር በደቡብ አፍሪካ ተመሰረተ!!


ጀግኖች አባቶቻችን በደማቸዉ የዋጇትን ኢትዮጵያ ሐገራችንን በክብር ለዘላለም ለማቆየት የአማራዉ መሐበረሰብ መሐበር በደቡብ አፍሪካ ተመስርቷል።
የአማራ መሐበረሰብ ማህበር የተሳኩ ዉይይቶችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በነዚሁ ወይቶች ላይ በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት ከህወሃት ወያኔያዊያን ባንዳዎች የጠራና የጸዳ አመራሮችን በማዋሃድ መሐበረሰቡን በትጋት የሚያገለግሉ የህዝብ ልጆችን በማቀራረብና ኢትዮጵያዊነትን በማስቀደም ” ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር” የሚል መሪ ሐሳብ በመያዝ በክብር በመደራጀት ላይ የሚገኘዉ የአማራ መሐብረሰብ መሐበር ሐገር የማዳንን እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ወገኖችን በማደራጀት ለወገኖቹ ጥቅምና ሰባዊ ክብር በብርቱ እንደሚታገልና በህወሃት ወያኔ የተነጠቅነዉን ህዝባዊ ማንነት ለማስመለስ እንደሚተጋ ተረጋግጧል።
በሲያትል የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ስኬታምና የተዋጣለት ዉይይት በማድረግ ኢትዮጵያዊነትን ኩራት ያደረጉ ጽንሰ ሐሳቦች ጎልተዉ ወጥተዋል።በተያያዘ ዜና በመላዉ አለም አማርድ በሚል መጠሪያ የተመሰርተ የጉራጌ ህዝቦች መሐበር በነገዉ እለት በደቡብ አፍሪካ ታላቅ ዉይይት መጥራቱን በኢትዮጵያዊነቱ ከማይደራደረዉ የጉራጌ ህዝብ ምንጭ ለማግኘት ያቻልን ሲሆን ህዝቦች በአንድነት በመደራጀት ሐገራቸዉን የማዳን እርብርቡ በየሐገሩ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ኬርቲና የጉራጌ ህዝቦች የሬዲዮ ጣቢያ የሙከራ ፕሮግራሞችን በማድረግ ላይ ይገኛል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ሎዑል አለሜ

No comments:

Post a Comment