Thursday, November 17, 2016

የማርክ ዙከርበርግ የማህበራዊ ድረ ገፅ አድራሻዎች ተሰረቁ


የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ የማህበራዊ ትስስር ገፅ አድራሻዎች ባለፈው አመት ግንቦት ወር በመረጃ መንታፊዎች መሰረቃቸው ይታወሳል።
በወቅቱ የትዊተር፣ ሊንክድኢን፣ ፒንትረስት እና ኢንስታግራም አድራሻዎቹ (አካውንቶች) ነበር የተሰረቁት።
የዙከርበርግ ፒንትረስት አድራሻ አሁንም ራሱን “አወርማይን” ብሎ በሚጠራ የመረጃ መንታፊ ቡድን በድጋሚ መሰረቁ ተሰምቷል።
“አወርማይን” የተሰኘው በሳኡዲ አረቢያ የሚገኝ የመረጃ ዘራፊዎች ቡድን አባላት ታዳጊዎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፥ ዋና አላማቸውም የታዋቂ ግለሰቦችን የማህበራዊ ሚዲያ አድራሻዎች ሰብረው በመግባት ለሌሎች ስለ ኢንተርኔት ደህንነት ግንዛቤ መፍጠር ነው ተብሏል።
ቡድኑ ለሲ ኤን ኢ ቲ በላከው መረጃም የዙከርበርግን የፒንትረስት አደራሻ (አካውንት) በድጋሚ ሰብሮ መግባቱን አስታውቋል።
ለዚህም ማረጋገጫ እንዲሆን የፒንትረስት ፕሮፋይል ምስሉን “ሃክድ” የሚል ፅሁፍ ጨምረውበታል።
ቡድኑ የዙከርበርግን ፒንትረስት አድራሻ እንዴት መስበር እንደቻለ አልገለፀም። ይሁን እንጂ በዚህ አመት በጥቁር ገበያ የተለቀቁትን የማህበራዊ ሚዲያዎች አድራሻዎች ስሞች እና የይለፍ ቃሎች በመግዛት የፒንትረስት አድራሻውን አለመስበራቸውን አስታውቀዋል።
“አወርማይን” የዙከርበርግን የትዊተር አድራሻ ስም እና የይለፍ ቃልም ይፋ አድርጓል።
ቡድኑ የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ የአሁኑ የትዊተር አድራሻው የይለፍ ቃል ከቀድሞው የጂሜል አድራሻው የይለፍ ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው።
የቡድኑ አባላት ባለፈው አመት ሀምሌ ወር ላይም የፖክማን ጎ ሰርቨርን ሰብረው የገቡ ሲሆን፥ የአሜሪካውን የሶፍትዌር ኩባንያ ኒያንቲክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆን ሀንኬ የትዊተር አድራሻ መስረቅ ችለዋል።
የማርክ ዙከርበርግ የማህበራዊ ድረ ገፅ አድራሻዎች ተሰረቁ
“አወርማይን” ከስድስት ወራት በፊት የትዊተር ዋና ስራ አስፋፃሚ ጃክ ዶርሲ እና የጎግል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሱንድራ ፒቻይን የማህበራዊ ትስስር ገፆች መመንተፉን ማስታወቁ የሚታወስ ነው።
ቡድኑ ባለፈው አመት ግንቦት ወር የዙከርበርግ የትዊተር እና ፒንትረስት አድራሻ ሰብሮ ሲገባ የሁለቱም የማህበራዊ ትስስር ገጾቹ የይለፍ ቃል “dadada” የሚል እንደነበር መግለፁ አይዘነጋም።
የዙከርበርግ በመረጃ መንታፊዎች እጅ መውደቅ ሁሌም እንደምንለው የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ደህንነት ለመጠበቅ ጥንቃቄያችን እጅጉን መጨመር እንደሚኖርበት ያመላክታል።

No comments:

Post a Comment