Thursday, November 3, 2016

የፖለቲካ ጥላቻ ለለውጥ በሚደረገው ሂደት ላይ ችግር ስለሚፈጥር በጊዜ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው።


የፖለቲካ ጥላቻ ለለውጥ በሚደረገው ሂደት ላይ ችግር ስለሚፈጥር በጊዜ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው። ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
የሕዝብ ማንዴት ያሌላቸው ፖለቲከኞች ራሳቸውን የሕዝብ ወኪል አሊያም በሕዝብ የተቀቡ አድርገው ሲያቀርቡም የፖለቲካ እብደቶች እየገነኑ ይመጣሉ::በሃገራችን ፖለቲካ ውስጥ የሚታዩ የፖለቲካ ጥላቻ ምቀኝነት ግለኝነት ቅናት የመሳሰሉት ለውጡ በእንብርክክ እያስኬዱ የሚገኙ ሲሆን ሂደቶን ሁሉ ባለህበት እርገጥ ሆነዋል:: እንደኔ እምነት ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት ክፋት እና ግለኝነት የጎሳ እና ከፋፋይ ፖለቲካ የሚከተለ እንደ ሕወሓት ያሉ ድርጅቶች ያነገቡት አርማ ነው::መልካም እና ጽኑ ታጋዮች እንደተጠበቁ ሆነው በስለናል የትግል ልምድ አለን ከሚሉ ፖለቲከኞች ጀምሮ እዚህ ግቡ የማይባሉ ገደል ማሚቱዎች ድረስ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቦርቅቀው ለማተራመስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም::ከኛ በላይ ላሳር የሚሉ እንጭጭ ፖለቲከኛ ነን ባዮች ጥቂቶች ሰፊዉን ሜዳ በተግባር ኣልባ ፕሮፓጋንዳ ብቻ አጣበዉት ሌላው እጁን አጣጥፎ ሲያይ መመልከትም ግርምትን ይፈጥራል::የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሰከረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይህን ያህል ተተራምሷል ለማለት ግን አያስደፍርም::

No comments:

Post a Comment