Monday, November 14, 2016

ወያኔ የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን፤ ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው::


ወያኔ የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን፤ ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
 – Minilik Salsawi – mereja.com – ስምምነት የጎደለው ትግል ፣ መግባባት የተሳነው ፖለቲካ ፣ በጥላቻ ፖለቲካ የታጀለ ፕሮፕጋንዳ፣ ለጠላት የፖለቲካ ፍጆታ በሩን የበረገደ ጭፍን ኣስተሳሰብ፣ በድቦ የስድብ ፖለቲካ የሚያራምድ መንገኝነትን የለበሰ ባዶ ጩኸት ብዙ ማለት ይቻላል ለዲያስፖራው ፖለቲካ ። እነማን ማን እንዳደራጀቸው የነማን ግርፍ እንደሆኑ ለይተን የማናውቅ የማንነቃ ከትግል ይልቅ ኣፍ መክፈት የሚቀናን እጅግ ልንተች የምንገባ ንፋሳሞች ነን።ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው፥ከወያኔ የማይለይ ኣስተሳሰብ ያነገቡ የወያኔ ግልባጮች ትላንት በእንበታትነዋለን ዛሬ ደግሞ ጥያቄው የቅኝ ግዛት ነው በሚሉ ንፋሳም ኣጀንዳዎች መላተም ሊቆም ይገባል። ብስለት በጣም ያስፈልጋል።ተዋጠልህም አልተዋጠልህም እውነቱ ይህ ነው።
 
በየማህበራዊ ድህረገጹና በየዌብ ሳይቱ ከማውራት መሬት ላይ ወርዶ ተገባራዊ ስራ መስራት ይጠበቃል። ኢትዮጵያን እንበታትናለን ኣሊያም ጥያቄያችን የቅኝ ግዛት ነው የሚሉ ሃይሎችን ማኮላሸት የሚቻለው ተግቶ በመስራት እንጂ በማውራት ኣይደለም። የሚገርመው ስሜታውያን በርክተዋል::ተናግረው እፎይ ብለው የሚተኙ በርካቶች ሆነዋል::ልክ ልኩን ነገርጉት ብለው ሌላውን ደሞ ለማሸማቀቅ (የሚሸማቀቅ ካገኙ) አስበው በየምናምኑ የሚንጎዳጎዱ ጊዜው ይቁጠራቸው::በነፈሰበት የሚነፍሱ ሳያገናዝቡ የሚያራግቡ የፈጠራ እሳት የሚያርገበግቡ በተገኘበት ተደናብረው እና ደንብረው ደንግጠው ለማስደንገጥ የሚርበተበቱ እንዳሉ ሁሉ ሙድ ለመያዝ የሕዝብን ጭንቀት የሚጠቀሙበት ተደምረው ሆዳም በጥቅም የሚደለሉ በጠለዟቸው ሄደው የሚቾመሱ አጀንዳ እና አቋም አልባ ሮቦት ካድሬዎችም በርካቶች ሆነዋል::ይህ ሁላ የግንዛቤ እጥረት ነው::ያለንበትን ጊዜ እና የሚካሄዱ ትግሎችን አለመመዘን ለትግሉ አስታውጾ ለማድረግ ደፋ ቀና ከማለት ይልቅ ተደራሽነት ያሌላቸውን የክፋት ብእር አጀንዳዎችን ይዞ መክለፍለፍ ምም ውጤት የለውም::ለመድገም ያህል ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው::
 
ወያኔ ስራዋን ትሰራለች::ጓዳ ጎድጓዳ ገበናውን ስላወቀች በተላላኪዎቿ የሚሰጠውን የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች አሸክማ እሷ የውስጥ ጉዳይውን እያስተካከለች የለውጥ ሃይሎች እያሰረች እየሳደደች እየገደለች ስልጣኗን ታጠናክራለች::እና ከሚዘመሩ የሃሰት መዝሙሮች ተነስተን ወያኔ አብቅቶላታል በሚል የፕሮፓጋንዳ መደምደሚያ ላይ ትተን የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን::ራሳችን ማረም የምንጀምረው መች ይሆን ?አጀንዳ የማታጣው የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች ማዘጋጀት ስራዋ የሆነው ወያኔ የምታመጣው አጀንዳ እና የቤት ስራ አትኩሮት ባንሰእጠው ያላትን የፕሮፓጋንዳ ሂደት ማኮላሸት እንችላለን::
 
.. ኧረ በስንቱ ልበጥበጥ አለች? በሶ:: ይህንን የሚያራግቡ እና አገር ወዳዱን ርሁሩሁን ዲያስፖራ ሆዱን የሚያንቦጫብጩ አጀንዳዎች ላይ እንዲሽከረከር ማድረግ ምን ያህል የወያኔን አደገኝነት የሚያሳይ ነው::አደባባይ ላይ አተካራ ገጥሞ የለውጥ ሃይሎን በ ነው/አይደለም አተካሮ ለማናከስ ክርክሮችን ፈጥሮ አለመግባባቶች ለማስፋት የሚደረጉ ያልተጣሩ መረጃዎች እና የፈጠራ ማዘናጊያ ጽሁፎች ምን ያህል የትግሉን ወንዝ እንደሚያሻግሩን አላውቅም:;
 
መንገድ ዳር ሰጥሞ ለመቅረት ካልሆነ በስተቀር ወያኔያዊ የፈጠራ አጀንዳ እና መረጃ ላይ ፊት ለፊት እየነጠሩ መጠዛጠዝ የብስለት ስርቆት መካሄዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል::ወያኔን ለመጣል አንድ እና አንድ ነገር ያስፈልጋል ህዝብ ተስፋ የሚያስቆርጡ መረጃዎች የለውጥ ሃይሎች የእርስ በእርስ መናከስ በተገኘ አጀንዳ እንደተፈለገ ንፍስፍስ ማለት የመሳሰሉት ጉዳዮች ሊታሰብባቸው እና ሊወገዱ ይገባል::የሚመጡ መረጃዎች ሃላፊነት የሚወስድ ሰው አሊያም ሚዲያ እስካልተገኘ ድረስ አሊያም ወያኔን ወያኔ አዋረደ በሚል የዋህነት ፈሊጥ መነሳት እንዲሁም ባልበሰለ የዘረኝነት እና የመንደርተኝነት ጽሁፎች ከመቃጠል ራሳችን ማዳን እና ልብ መግዛት ይገባናል:: ሁላችንም በጋራ በሚደረጉ ትግሎች ላይ ልንረባረብ ይገባል::ትግሎችን በማስፋፋት በማስተማር እና በመቀስቀስ በመርዳት ላይ ልንሰማራ ይገባል:ብስለት ማለት ለትግል የሚደረጉ አስታውጾዎችን በማበርከት እና በተረጋገጡ አጀንዳዎች ላይ ስራ መስራት ሲቻል ብቻ ነው::እና እኔም እላለሁ ያለንበት ጊዜ በተገኘው አጀንዳ ላይ የሚነፈስበት ሳይሆን ብስለት የሚጠየቅበት ጊዜ ነው:: ‪#ምንሊክሳልሳዊ
በየማህበራዊ ድህረገጹና በየዌብ ሳይቱ ከማውራት መሬት ላይ ወርዶ ተገባራዊ ስራ መስራት ይጠበቃል። ተዋጠልህም አልተዋጠልህም እውነቱ ይህ ነው።

No comments:

Post a Comment