Saturday, November 19, 2016

አርጎባ ሰንቀሌ የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን መገደሉን ተከትሎ መውጫ መግቢያ ኬላዎች ተዘግተው በተኩስ በመናጥ ላይ ይገኛል።


አርጎባ ልዩ ወረዳ ደቡብ ወሎ መውጫ መግቢያ ኬላዎች ተዘግተው በተኩስ በመናጥ ላይ ይገኛል።
የአርጎባ ብሄረሰብ ዋና መቀመጫ ሰንቀሌ በፌደራል ፖሊስ ተወራለች ምክንያት የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን በታጣቂዎች በመገደሉ ። ለምን ከተባለ አንድ ሹፌርን ሊሞት እስከሚያጣጥር ድረስ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ሌሊት እንዲደበደብ በማድረጉና ጧት መንገድ ላይ ጥለውት በመገኘቱ። የልጁ እንዲህ መደረጉ ያስቆጣው የአርጎባ ህዝብ መሳሪያውን ወልውሎ ትናንት ጧት 2 ሰአት ኮሚሽነሩ ቤት በመሄድ እዛው ገድለው የሱንም አስክሬን መንገድ ላይ አውጥተው በመጣላቸው ትናንት ማታ ፌደራል ፖሊስ አካባቢውን በመውረር እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ ወንድ ሴት ህፃን ሳይሉ እየደበደቡ ነው ።
ዛሬ ጠዋት በደቡብ ወሎ ዞን በአርጎባ ልዩ ወረዳ ፣ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብረሀም በታጠቁ የህብረተሰቡ አካላት በጥይት ተደብድቦ መገደሉን ተከትሎ አካባቢው ወደጦር አውድማነት ተቀይሯል፡፡ እስከአሁኑ ሠአት ድረስ በመንግስት ሀይሎችና በነዋሪው መካከል ከፍተኛ ውጊያ በመካሄድ ላይ ሲሆን ከጥቃቱ ለመሸሽ በመሞከር ላይ ያሉ የመንግስት ሠራተኞችና ነዋሪዎች መውጫ ቀዳዳ አጥተው በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ተሠብስበው ጥበቃ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ያገረሸው ይህ ግጭት የተቀሰቀሰው ትላንት የዞኑ አስተዳዳሪ ከህብረተሰቡ ጋር ያደረጉት ስብሰባ ባለመግባባት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው፡፡ በአሁኑ ሠአት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመንግስት የፀጥታ ሀይል ከስፍራው የደረሰ ሲሆን የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ መውጫ መግቢያ ኬላዎች ተዘግተው ስፍራው በተኩስ በመናጥ ላይ ይገኛል።

No comments:

Post a Comment