ወታደሮች በየዩኒቨርስቲዎቹ ካምፕ እያቋቋሙ ነው
የተማሪዎችን ተቃውሞ አፍኖ ለመያዝ እንዲያስችል በሚል በርካታ ወታደሮች በየዩኒቭርሲቲዎቹ ግቢ ውስጥ እንዲሰፍሩ ተደርጓል፡፡ ይህ ድርጊት በዩኔስኮ የተደነገገውን የከፍተኛ ትምህርት ነፃነት የሚገፍ በመሆኑ ሊወገዝና ሊጋለጥ ይገባዋል ተብሏል፡፡
የተማሪዎችን ተቃውሞ አፍኖ ለመያዝ እንዲያስችል በሚል በርካታ ወታደሮች በየዩኒቭርሲቲዎቹ ግቢ ውስጥ እንዲሰፍሩ ተደርጓል፡፡ ይህ ድርጊት በዩኔስኮ የተደነገገውን የከፍተኛ ትምህርት ነፃነት የሚገፍ በመሆኑ ሊወገዝና ሊጋለጥ ይገባዋል ተብሏል፡፡
ምንም እንኳ ወያኔ የጦር ሜዳ ትጥቅ የታጠቁ ወታደሮችን በየዩኒቭርሲቲ ጊቢዎች ውስጥ ቢያሰማራም በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት በአምቦ፣ በወለጋ፣ በነጆ፣ በጂማ ዩኒቭርሲቲዎች “የታሰሩት ይፈቱ” በሚል መሪ ቃል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ከደረሱን መረጃዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡
በርካታ ተማሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፣ እየታፈኑ ወደ አልታወቁ እስር በቶች ተወስደዋል፡፡ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ ከቤተ መጸሀፍቶችና ከጥናት ክፍሎች ውጪ ሲንቀሳቀሱ የሚገኙ ተማሪዎች እየተደበደቡ መሆናቸውን ተማሪዎች በምሬት ሲገልጹ ተሰምተዋል።
No comments:
Post a Comment