Monday, November 14, 2016

የሰማያዊ ፓርቲ ኣዲሱ ሊቀመንበር የሕወሓትን የሚኒስትሮች ሹም ሽር በበጎ የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ ኣሉ።


Image result for yeshiwas assefaየሰማያዊ ፓርቲ ኣዲሱ ሊቀመንበር የሕወሓትን የሚኒስትሮች ሹም ሽር በበጎ የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ ኣሉ።
ኣቶ የሽዋስ ኣሰፋ በአዲሱ የሕወሓት ሹም ሽር ዙሪያ ኣዲስ ኣድማስ የተባለ ጋዜአጣ ላቀረበላቸው ጥያቄ የሚኒስትሮች ሹም ሽር በበጎ የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡መንግስትም ምላሽ ለመስጠት እየሞከረ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በማለት የገለጹ ሲሆን በምን ኣይነት ሚዛን ይህንን ሊሉ እንደቻሉ ኣስገራሚ ሆኗል፤ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሌአጅ የፓርቲ ኣባላይ የሆኑና ኣባል ሳይሆኑ በደጋፊነት ያሉ ሰዎችን ሰብስቦ ሚኒስትር ኣድርጎ የሾመውን ሕወሓት በጎ ስራ ሰራ ብሎ ማንቆለጳጴስ የኣቶ የሽዋስ ኣሰፋ የፖለቲካ ኣለመብሰል ያሳያል ሲሉ ኣስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ኣዲስ ኣድማስ ጋዜጣ በቅዳሜው እትሙ ላይ ኣቶ የሽዋስ ኣሰፋናን ኢንጂነር ይልቃል ኣሰፋን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኣድርጎ ሁለቱንም ያቀረበ ሲሆን ሰማያዊ ፓርቲ ለሁለት መከፈሉ ፍንጭ ሲሰጥ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትን ስለ ኣሜሪካ የትራምፕ ማሸነፍ ኣቶ የሽዋስን ስለ ሕወሓት ሹምስር ማናገሩን ይጠቁማል።ኣቶ የሽዋስ ከኣንድ ኣመት በላይ ታስረው የተፈቱ ሲሆን በእስር ቆይታቸው ከወያኔ የፖለቲካ ተሃድሶ መውሰዳቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ ወዲያው ከእስር እንደተፈቱ በሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርነት ድንገት በመፈንቅለ ወንበር መሾማቸው እስካሁን ግራ ኣጋብቷል።

No comments:

Post a Comment