Tuesday, November 29, 2016

የአማራ ህዝብ የተጋረጡበት አደጋዎች ባለ ፈርጀ ብዙ ናቸው ። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ – ኄኖክ የሺጥላ


የአማራ ህዝብ የተጋረጡበት አደጋዎች ባለ ፈርጀ ብዙ ናቸው ። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ
1) የአማራ ህዝብን በአንድነት ለማደራጀት እና በህብረት እንዲቆም እየተደረገ ላለው ጥረት ከዚህ በፊት አማራ አይደለንም ሲሉ ያልተሰሙትን የአማራ ህዝብ ክፋይ የሆኑትን አካሎች ፥ እንደ አገው እና ቅማንት ያሉ ማህበረሰቦችን ( ህዝብ ባልወከላቸው ተወካዮቻቸው አማካኝነት ) አማራ አይደለንም የሚል ወያኔያዊ አጀንዳ እንዲያነሱ በማድረግ እና የአማራ ህዝብ ህብረት የነርሱ ህልውና ላይ አደጋ ሊጥል የሚችል ጠንቅ እንደሆነ በመስበክ አማራውን እንደ ቁጠባ ቤት በተርታ በመከፋፈል በአንድነት እንዳይቆም የማድረግ ስራ እና ሴራ
2) አማራን በአረንጓዴ ፥ ቢጫ እና ቀይ ሰንደቅ አላማችን እያታለሉ ፥ አማራ የሚያምርበት ኢትዮጵያዊነት ነው በማለት ፥ በኢትዮጵያዊነቱ የማይታማውን የአማራ ህዝብ ፥ ለተራ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል ብቻ ፥ የአማራ ህዝብ ስቃይ በገሃድ እየታየ « ኢትዮጵያዊነትህን እንዳትለቅ ብቻ ሳይሆን ፥ ኢትዮጵያዊነትህን ይዘህ ጥፋ» በሚል ሰበካ የአማራን ህዝብ ተክለ ሰውነት ማቀጨጭ እና ጥሪቱን መሞለጭ!
3) በኖርንበት እና ባየነው ፥ ምስክርም በምንሆንበት 25 አመት የወየኔ ዘመናት ፥ አንድም ኢትዮጵያዊ ( ከአማራ በስተቀር ) ከየትኛውም ክልል ሳይባረር ፥ አመራ ግን በዘሩ ሲባረር ፥ ስለዘሩ ሲሳደድ እና በዘሩ ምክንያት ሲገደል እያየነው ፥ ይህንን ህዝብ ለመታደግ የሚደረገውን ርብርብ በዘረኝነት በመፈረጅ ፥ ታሪክን ተገን አድርጎ ፥ የዛሬይቱን ኢትዮጵያ በማይወክል መልኩ አማራ ራሱን ጨፍልቆ ፥ ከሱ በቁጥርም ይሁን በእውቀት እጅግ ባነሱ አካሎች ተወክሎ ፥ ከስራቸው እንዲንደፋደፍ ፥ ስለት እና ምልጃ እንዲያቀርብ ፥ ራሱን ክዶ ፥ በራሱ በአማራ አጋፋሪዎች በተደረገ የኤሌሎች በአለ ሲመት ላይ አክሊል አቅራቢ ፥ ምንጣፍ አንጣፊ ፥ የዙፋን እግር ወልዋይ እና ሰረገላ ገፊ እንዲሆን እየቴሰረ መሆኑ
4) የአማራ ህዝብ ከብቱን ሽጦ ፥ ደሙን ገብሮ ፥ ልጆቹን ሰውቶ የሚያደርገውን ትግል በጠራራ ፀሃይ ፥ ባልተወከሉ ታጋዮች ትግሉን ተቀምቶ ፥ ለሞቱ ስም ተሰጥቶት ፥ ለትግሉ የሃሰት ዜና ተሰርቶለት ፥ ባልዋለበት ውሎ እና ላልቆመለት አካል ቆሞ ፥ የክብር ሞቱ መነገጃ እና መወስለቻ ሆኖ እያየም ፥ ስድብ እና ክብረ ነክ የሆኑ ትችቶችን ፈርቶ ፥ ከጥቂቶች እውነት ይልቅ ለብዙሃን ነውር ገብሮ ፥ እውነቱን እያወቀ ፥ የሆነውን እያየ ፥ ሞቱን አማራ ለነፃነቱ ሲል ያደረገው እንደሆነ ያልመሰከረ እና ያልተናገረ አማራ ባለበት ዘመን መፈጠራችን እና መኖራችን
5) ከትግሉ ባሻገር ትግሁ አማራ ማንነቱን ጥያቄ አድርጎ ሲነሳ ፥ ወልቃይት አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም በሚል የፋኖ መለከት የተቀጣጠለው ትግል ፥ በውጭ ሃገር አርባ ስም ተሰጥቶት ፥ የትግሉ አብሪ ጥይት አማራነት እንደሆነ እየታወቀ ፥ የጎጃም ገበሬ ለጎንደሩ ገበሬ መገደል ባህር ዳር ላይ ሲሞት የሞተው ጎጃሙን እና ጎንደሩን አንድ ያደረጋቸው አማራ መሆናቸው ፥ ባንድነትም ያቆማቸው ይኸው አማራነታቸው እንደሆነ ለሳር ለቅጠሉ ሳይቀር ግልፅ በሆነበት ሰዓት ፥ ይህ የአማራ ትግል ሰላም የነሳቸው ፥ ሲቻል የአማራ ህብረትን ኒዩክሊየር ቦምቦ አስመስሎ በመሳል ሳይቻል ደሞ አማራን በምክንያት በመሰነጣጠቅ ፥ ጎንደር ህብረት ፥ ጎጃም ህብረት ፥ ወሎ ህብረት ፥ ሸዋ ጅብረት እያሉ ሃይሉን ለመበታተን ፥ ገባሪነቱን ዘመን ተሽጋሪ ለማድረግ ፥ ሃይሉን ለመፈረካከስ ፥ የህብረት ክሩን ለመበጠስ ፥ የአንድነት ዋልታውን ለመከስከስ እየሄዱበት ያለው መንገድ በራሱ በአማራው ተወላጅ ሳይቀር በከፊልም ቢሆን ተቀባይነት ማግኘቱ ይመስለኛል ።
ጥያቄ አለኝ ፥ የጎንደርን አማራ በጎንደር ህብረት ፥ የጎጃሙን በጎጃም ፥ የወሎውን በወሎ ፥ የሸዋውን በሸዋ ጠቅልለን ፥ ሰብረን እና ሰንጥቀን ከጨረስን ወዲያ ፥ በሃረርጌ የሚኖሩን የወሎ አማሮችን የሃገረርጌ ወሎዬውች ፥ በጅማ የሚኖሩ የጎንደር አማሮችን የጅማ ጎንደሮች ፥ የ ወለጋ ጎጃሞች ፥ የአዲስ አበባ ሸዋዎች ብለን ሌላ የአማራ ህብረት ልንፈጥር ነው ?
አማራ እንዲበረታ አማራ በህብረት ይቁም! የአማራ ድል በአማራ ህብረት ብቻ የሚገኝ ነው! የብሄር ፖለቲካ የነገሮች ሁሉ መለኪያ በሆነበት ዘመን ፥አማራ አይደራጅ ማለት አማራን በጀርባው በኩል እንደ ማረድ ነው !
አማራ ንቃ!
ኄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment