Monday, November 28, 2016

በአየር ንብረትና በአካባቢ ብክለት የሚታወቀው ወያኔ በሞሮኮው ስብሰባ የአፍሪካ ወኪል ሆኖ መቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል


በአየር ንብረትና በአካባቢ ብክለት የሚታወቀው ወያኔ በሞሮኮው ስብሰባ የአፍሪካ ወኪል ሆኖ መቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል
ባለፈው ሰሞን በአየር ንብረት ለውጥ በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ ላይ ዓለም አቀፍ ጉባኤ መካሄዱ ይታወቃል፡፡ ወያኔም በዚህ ስብሰባ ላይ ከእራሱም አልፎ የሌሎች አፍሪካ ሀገራትም ወኪል ሆኖ መቅረቡን ሲለፍፍ ከርሟል፡፡ በአየር ንብረት ብክለት ወንጀለኛ የሆነው የወያኔ አገዛዝ በዚህም ስብሰባ መገኘቱም ሆነ ሌሎችን መወከሉ ብዙዎችን አስገርሟል። በዚህ በወያኔ 26 ዓመት የግፍ ዘመን ደኖች ተጨፍጭፈዋል፣ የዱር አራዊቶች እየተሰደዱ ወደ ጎረቤት ሀገራት እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡
የጋምቤላ ድንግል መሬትን ለህንድ፣ ለአረብ፣ ለቻይና፣ ለወያኔ ኮሎኔሎችና ጀነራሎች በመለገሱ የጋምቤላ የተፈጥሮ ደን ተጨፍጭፎ በምንጮች ብዛት የሚታወቀው መሬት ምድረ-በዳ ሆኗል፡፡ በአየር ብክለት የሚታወቁ ፋብሪካዎች ከቻይና እየተነቀሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲተከሉ በመደረጉ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ በመርዛም አየር ብክለት በዓለም የመጀመሪያ ደረጃን ልትይዝ እንደምትችል ብዙዎች ይገምታሉ፡፡
አብዛኛዎቹ ወንዞች ከፋብሪካዎች በሚወጡ ዝቃጮች ተበክለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ቀደም ብሎ አሳ ይጠመድባቸው የነበሩት እንደ ቀበና፣ አቃቂና የመሳሰሉ ወንዞች በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ የተበከሉ ከመሆናቸው ሌላ እንኳን የአሳ ምንጭ ሊሆኑ በከተማዋ ተስፋፍቶ ለሚገኘው በሽታ ምንጭ መሆናቸውን ብዙዎች በምሬት ይናገራሉ።ተማሪዎች በክፍል ውስጥ እየተማሩ በጠኔና በተበከለ አየር እየተልፈሰፈሱ እንደሚወድቁ በተለያዩ ጊዜያት መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ Finote Democracy

No comments:

Post a Comment