Monday, November 14, 2016

ጀግኖቹ የእንቃሽ አርበኞች በቄስና ሽምግልና ስም ወያኔ የሞከረውን አክሽፈው አሁንም ጠላትን እንደገጠሙ ነው።


Achamyeleh Tamiru's photo.
አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ከእንቃሽ
እንቃሽ የተፈጠረው ፍልሚያ በአማራ ተጋዳዮችና በትግራይ ነፍሰ በላ መከላከያ መካከል የነበር ሲሆን ተጋዳዩ ህዝባችን የወያኔን የመከላከያ ካምፕ በማፈን ዶግ አመድ አድርጎታል። ከሁለቱ ወገን ስለደረሰው ጉዳት እያጣራን ነው።
አምስተኛ ቀኑን በያዘው በዚህ የእንቃሽ ጦርነት የተበሳጨው ወያኔ ያለ የሌለ ኃይሉን ወደ ስፍራው በመላክ መላ ህዝቡን ለመጨረስ ከበባ በማድረግ ላይ ስለሆነ ይህንን ለመመከት በጀግንነት እየተዋጋ ያለው የገበሬ አፋጣኝ ትብብር ከቅርብም ከሩቅም ላለ ወገን አቅርቧል።
☛ በተለይም በጃኖራ፣ በአጅሬ፣ በቆላ ወገራ ያለው ወገን በፍጥነት እንዲደርስ።
☛በኪንፋዝ በለሳ ያለው ወገን አቆራርጦ እንዲደርስ።
☛በቆላ መረባና በመሬና ያለው ወገን ደግሞ በበርሃው አቋርጦ ለከበባ እየመጣ ያለ የአጋዚ ሃይል ስላለ እዛው እንዲያስቀሩት።
☛የዳባት የገደብጌ የአምባ ጊዮርጊስ ወጣት መንገድ በመዝጋት መረጃ በመለዋወጥና ጠላትን በያለበት በመወጠር ትብብራቹህ እንዳይለየን ብለዋል።
ጀግኖቹ የእንቃሽ አርበኞች በቄስና ሽምግልና ስም ወያኔ የሞከረውን አክሽፈው አሁንም ጠላትን እንደገጠሙ ነው። ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ቤተዘመድ ያላችሁ ጉዳዩን እየደወላችሁ ለወገን ደራሽ እንዲሁን አስተባብሩ። ጥሪው ለሁሉም እንዲደር ይሁን።
Achamyeleh Tamiru's photo.

No comments:

Post a Comment