Monday, November 28, 2016

የኤች አይቪ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ – ቁንጮ የወያኔ ባለስልጣኖች በበሽታው የተለከፉ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ።


የኤች አይቪ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ
የኤች አይ ቪ ህሙማን ቁጥር መቀነሱ በተነገረ ማግስት ባስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ መሄዱ ይፋ ሆነ፡፡ የሀሰት መረጃ በመደርደር የኤች አይ ቪ ህሙማን ቁጥር መቀነሱን ባለፈው አመት መገለጹ የሚታወስ ሲሆን ይሀንን የሀሰት መግለጫ በርካታ በህመሙ ዙሪያ እውቀቱ ያላቸው ወገኖች በሽታው ባስደንጋጭ ሁኔታ ወጣቶችን እያጠቃ መሆኑን በየአጋጣሚዎቹ ማሳወቃቸው አይረሳም፡፡
ይህ ህመም በአሁኑ ሰዓት የዩኒቭርሲቲና የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን እያጠቃ መሆኑን በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጥናት ያካሄዱ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በዝሙት ሥራ ላይ ከተሰማሩ ሴቶች ውስጥ ከአራቱ ሦስቱ የበሽታው ተጠቂዎች መሆናቸው የተደረገው ጥናት ቢያረጋግጥም በወያኔ መመሪያ ከአራት ሴቶች አንዷ ብቻ በበሽታው ተጠቂ እንደሆነች ይጠቁማል፡፡ በፖለቲካ ቆሻሻ የበከተው ወያኔ ፊቱን በርሜል ሙሉ ቫዝሊን ቢቀባም እንደማይወዛ የሚገልጹ ወገኖች አገዛዙ በስልት ወጣቱን በአደንዛዥ እጽ ሱሰኝነት፣ በአልኮል ጠጪነት፣ በዝሙት እንዲልከሰከስና በራስ መተማመን እንዳይኖረው ጥረት እያደረገ ነው ይላሉ። ቁንጮ የወያኔ ባለስልጣኖች ስብሀት ነጋንና ሳሞራን ጨምሮ በበሽታው የተለከፉ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ። 

No comments:

Post a Comment