Sunday, November 20, 2016

ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣን ሳውዲ አረቢያ ይመጣሉ (ነቢዩ ሲራክ )


* ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣን ሳውዲ አረቢያ ይመጣሉ (ነቢዩ ሲራክ )
* የሪያድ ኢንባሲ ዝግጅት ላይ ነው
* የሰራተኛና አሰሪ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል
* አብዛኛው ነዋሪዎች ስምምነቱን ” ሌላ አደጋ ነው “ሲሉ ይቃዎሙታል
* አንዳንድ ነዋሪዎች ስምምነቱ “ብቸኛ አማራጭ ነው ይሉታል
የሚመጡት ከፍተኛ ኃላፊና የአቀባበል ዝግጅቱ …
================================
አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣን ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ይገባሉ ተብሎ በመጠበቅ ላይ መሆኑን ታማኝ መረጃዎች ከቀናት በፊት ደርሰውኝ የነበረ ሲሆን ይህንኑ መረጃ የሚያረጋግጡ ተጨማሪ የመረጃ ምንጮች ማምሻውን ደርሶኛል ። ከሪያድ እንደ ደረሰኝ የመረጃ ምንጮች ከሆነ ዛሬ ወይም በቀጣይ ቀናት ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መሆናቸውን ጠቁመዋል ።
ከቀናት በፊት ጀምሮ ከፍተኛ ባለስልጣን በሚል የሪያድ ኢንባሲ ከፍ ያለ ዝግጅት ማድረጉም ይጠቀሳል ። እንግዳው ይመጣሉ ተብሎ ዝግጅቱ በመደረግ ላይ ባለበት ሁኔታ ወደ ሀገር ቤት አቅንተው የነበሩት በሳውዲ አረቢያ ሙሉ የኢትዮጵያ መንግሥት አምሳደር አሚን ከሀገር ቤት በሳምንቱ መገባደጃ ወደ ሳውዲ ሪያድ ተመልሰው እንግዳቸውን የመቀበል ዝግጅቱን በመከታተል ላይ መሆናቸው መረዳት ተችሏል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የጅዳው ቆንስል ተጠሪ አምባሳደር ውብሸት ደምሴም እንግዳውን ለመቀበል ዛሬ ማታ ሪያድ መታዬታቸው ታውቋል ። ለተመሳሳይ አቀባበል ከቋታር ፣ ከአረብ ኢምሬት ፣ ከኩዌትና ከአጎራባች የአረብ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንባሲና ቆንስል ተወካዮች ይመጣሉ የተባሉትን ባለስልጣን ለመቀበል ሪያድ የገቡና ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁ መረዳት ብችልም ይህን መረጃ ማረጋገጥ አልቻልኩም !
አዲሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስላጣናትን ይዘው ወደ ሳውዲ ይመጣሉ ተንለው የሚጠበቁት ከፍተኛ ባለስልጣን በሰራተኞች ስምምነት ዙሪያ ለመስማማት ረዥም ጊዜ የወሰደውን የሰራተኛና አሰሪ የሁለትዮሽ ስምምነት በይፋ ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከዚሁ በተጨማሪ በኢኮኖሚ ፣ የገበያ ትስስርና በጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎም ይጠበቃል ።
የስደተኛው ነዋሪ ስጋት …
================
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዝግጅቱ አልቀደመምና ዳግም እንዳናነባ በሚል ነዋሪው በተለይም ከሰራተኛና ሰራተኛ የሁለትዮሽ ስምምነቱ በፊት መሰራት ያለባቸው ስራዎች አልተሰሩም በሚል ተቃውሞ በተደ ጋጋሚ ለመጡት ባለስልጣናት ማሰማታቸው ይጠቀሳል። እንኳ አዲስ የኮንትራት ሠራተኞች መጥተው በሳውዲ ሪያድ ኢንባሲና የጅዳ ቆን ስል መሥሪያ ቤቶች ከዚህ ቀደም ለመጡት ሰራተኞች ጥበቃ አለ ማድረጋቸው በገሃድ እየታወቀ ሌላ ሰራተኛ ለማስመጣት መስማማቱን ነዋሪዎች አጥብቀው ይነቅፉታል ። ሰምምነቱን አሳሳቢ የሚያደርገው በሳውዲና በተለያዩ አረብ ሀገራት ያሉ ዲፕሎማቶች የህገ ወጦችን ቀርቶ ከዚህ ቀደም በኮንትራት ሠራተኛና አሰሪ ስምምነት ሲደረህ የቪዛ ውል ማስፈጸሚያ ገንዘብ እየሰበሰቡ ባጸደቁት ውል ላይ የተ ጻፉት ስምምነቶች የዜጎች ይዞታ የመከታተ ልና የማስፈጸም ኃላፊነ ትን ሲወጡ አለመታየቱም ስምመነቱ እውነት የሚደረግ ከሆነ አሳሳቢ ያደርገዋል።
አስተያየት ሰጭዎች በማከልም በተለየዩ የሳውዲ ከተሞችና ገጠሮች ቀርቶ ከጅዳና ሪያድ ወጣ ብለው ለሚገኙ ዜጎች በኢን ባሲና በቆንሰል መ/ቤቶች የፓስፖርት ማደሻ ውክልና የመሰለውን አገልግሎት ለዜጎች የሰው ሃይል ችግር አላፈናፍን ባለው ሰዓት ተጨ ማሪ ሠራተኞች ሲመጡ በዜጎች የሚደርሰውን የመብት ጥሰት እንደ ሚያለፋው የሚናገሩ በርካታ ናቸው ። ሌላው የሰራተኛ ሁለትዮሽ ስም ምነት ረቂቁ ሲቀርብ በባለድርሻ ስደተኛኞች ግልጽና ጥልቅ ውይይ ት ሳይደረግ በጸደቀው አዋጅ የሚመጡት ዜጎች ጉዳይ ግልጽና ጥልቅ ውይይት አለመደረጉ ይጠቀሳል ።
ከሰምምነቱ ጋር በተያያዘ አስተያየት የሚሰጡ አንዳንድ ነዋሪዎች ከአቅም በላይ የናረውን ኑሮ መገፈት ላልቻለውን በኑሮ ውድነት ፣ በድህነት እና የመልካም አስተዳደር እጦት መድልኦና ፖለቲካው በፈጠረው ችግር ተዘፍቀው ለሚማቅቁ ዜጎች ስምምነቱ አማራጭ የለውም በሚል ስምምነቱን ይደግፉታል ። ከዚህ ቀደም የመጡት የኮንትራት ሰራተኞች የሰሩበትን ደሞዝ ሲነጠቁ ፣ ለከፋ ህመምና በተለይም ለአዕምሮ ህመም ሲዳረጉ ፣ ህጋዊው ነዋሪ የረባ የመብት ጥበቃና ግልጋሎት አለማግኘቱን የሚናገሩት እኒህ ነዋሪዎች ስደቱን በመከራው የባህር እና የበርሃ ጉዞ ሳይቀር ለሚቀላቀሉት ዜጎች ስምምነቱ አደጋ ቢኖረውም የተቸገረው ነዋሪ ብቸኛ አማራጭ ስምምነቱ መሆኑን ይናገራሉ ። ” ከኢትዮጵያ ኑሮ የሳውዲ ስደት ይሻላል ” የሚሉት እኒህ ነዋሪዎች መንግስት በተስፋ መቁረጥ የመከራውን ስደት በህጋዊ መንገድ ለመቀላቀል ለቆረጡ ግፉአን ዜጎች የመብት ጥበቃ ይተጋ ዘንድ መንግስትን ይማጸናሉ !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 11 ቀን 2009 ዓም
Image may contain: 4 people , suit

No comments:

Post a Comment