Monday, November 14, 2016

ሹም ሽሩ የህዝብ ተቃውሞ ውጤት ቢሆንም የፖሊሲ ለዉጥ ከሌላ ፋይዳ አይኖረም- የሰማያዊ ለቀመንበር የሺዋስ አሰፋ


የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ገዢው ፓርቲ የካቢብኒ ለዉጥ ለማድረግ ኡየተገደደው በሕዥብ ጫና ምክንያት መሆኑን ገልጸው፣ የካቢኔ ለዉጡ ግን መሰረታዊ የፖሊሲ ለዉጥ እስካላመጣ ድረስ ግን ምን ፋይዳ እንደሌለው ገልጸዋል።
“ሹም ሽሩ የህዝብ ተቃውሞ ውጤት ነው”
የሸዋስ አሰፋ
(የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)
በመጀመሪያ ደረጃ ይሄ ሹም ሽር የመጣው በህዝብ ተቃውሞ ምክንያት ነው፡፡ በህዝቡ መቶ በመቶ ተመረጥኩ ቢባልም፣ ህዝቡ ጥያቄ አንስቶ ካቢኔ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ እስከ መለወጥ ተደርሷል፡፡ የህዝቡ ዋነኛ ጥያቄ የፖሊሲ ለውጥ ነው። መሰረታዊ የስርአትና የፖሊሲ ለውጥ እንጂ የሰዎች ሹም ሽር አይደለም፡፡ ስለዚህ መልሱ ከጥያቄው በተቃራኒ ነው፡፡ ሁለተኛ አዲሶቹ ሰዎችም ቢሆኑ እዚያው አብረዋቸው የነበሩ፣ በስርአቱ ፖሊሲ የተጠመቁ ናቸው፡፡
አሁን ትምህርታቸው ነው እንደ ትልቅ ነገር ሲጠቀስ የነበረው፡፡ ነገር ግን ሀገሪቱ ላይ የተማረ ሰው ስለጠፋ አይደለም፤የማያሰራ ሁኔታ ስላለ እንጂ፡፡ ብዙ ችግር የተፈጠረው ሹመቶች ችሎታንና እውቀትን ሳይሆን ጎሳን፣ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ስለነበሩ ነው፡፡
እንደኔ እንደኔ የነበሩትን ሰዎች አስቀምጠው፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ቢያደርጉ የተሻለ ይሆን ነበር። አሁን ግን ዝም ብሎ የሰዎች ለውጥ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ከሚኒስትርነታቸው የተነሱ ሰዎች ምን ሆነው ነው የወረዱት? የሚለው አልታወቀም፡፡ በምን ጥፋት ነው? በምን ድክመት ነው? ይሄ መታወቅ አለበት፡፡ ያጠፋውም መቀጣት ይገባዋል፡፡ ለፖሊሲው ለውጥ መልሱ የሰው ለውጥ ነው የሆነው። በዚህ ምክንያት እኔ ብዙ ለውጥ አልጠብቅም፡፡ ግን አሁን የተደረገው ለውጥ ሁሉ የህዝቡ ትግል ውጤት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ መንግስትም ምላሽ ለመስጠት እየሞከረ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን በፍጥነት ወደ መሬት ማውረድ፣ የእውነት ማድረግ ይጠበቅበታል። የምርጫ ስርአቱ ይሻሻላል የተባለው ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ፣ እኛም ስንጠይቀው የነበረ በመሆኑ በበጎ የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment