በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመጽ አንድ ዓመት ሞላው። በኢትዮጵያ ትልቁን ቁጥር ለሚይዘው የኦሮሞ ማኅበረሰብ የተቃውሞ መነሻ የሆኑት የፖለቲካ ነፃነት እና ፍትሃዊ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄዎች ዛሬስ ተመልሰው ይኾን? የአሜሪካ ድምጿ ማርታ ቫንዶርፍ ከብራስልስ ባጠናቀረችው ዘገባዋ ታነሳዋለች።
ዋሽንግተን ዲሲ — በኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመጽ አንድ ዓመት ሞላው። በኢትዮጵያ ትልቁን ቁጥር ለሚይዘው የኦሮሞ ማኅበረሰብ የተቃውሞ መነሻ የሆኑት የፖለቲካ ነፃነት እና ፍትሃዊ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄዎች ዛሬስ ተመልሰው ይኾን? በዚህ ዘገባ ተካቷል።
በሌላ በኩል የኦሎምፒክ የማራቶን የብር ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ለሊሳ ፈይሳ፣ የግንቦት ሰባቱ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዶ/ር መረራ ጉዲና በብራስልስ አውሮፓ ሕብረት ጽ/ቤት ተገኝተው ለኅብረቱ የፓርላማው አባላት በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ነው ያሉትን የመብት ጥሰትም አብራርተዋል።
No comments:
Post a Comment