Tuesday, November 29, 2016

የደፈረሰው ፖለቲካችን የወያኔና የተቃዋሚዎች ስርስር የግብጽና ኤርትራ የኮማንድ ፖስት ምስረታ እቅድ በጆሮ የሰማናቸው ናቸው::

ተልባ በጥባጯ እያለች ጎበን በጣሿ ምች የተመታችበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኣሁንም ምኑንም ሳይመልስ ምናምኑን እንዳግበሰበሰ ቀጥሏል። ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱም ግፊቱ ቀጥሏል።የሚገርመው እያሰረ እየገደለ እያፈነ እያሳደደ ያለው አካል ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ስለ ሰብዓዊ መብት ለመነጋገር ሶስት ቀን ስብሰባ የሚቀመጥበት ግርግር ምን ያህል በሕዝብ ላይ እየተቀለደ እንዳለ እያየን ሲሆን ኮማንድ ፖስቱ እየሰራ ያለው ግፍ እና በሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን አደጋ ለመደገፍ ካልሆነ በቀር በፍጹ ስለ ሰብዓዊ መብት የሚቆረቆር ይገኛል ማለት ሞኝነት የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ስልጣን ኣካፍሉን ለማለት ካልሆነ በቀ ስብሰባው ከጭብጨባ የሚዘር ፋይዳ ኣይሰራም ወያኔ ተቃዋሚዎችን ተርታ የምጸበስበው አንድም ለማዘናጋት ኣሊያም አዲስ የፖለቲካ ፍጆታና ሴራ ከማለም የዘለለ ስራ የለውም። የሚገርመው ግብጽና ኤርትራ በካይሮ አሸባሪነትን የሚቆጣጠር በቀይ ባህርና ለምስራቅ ኣፍሪካ የሚያገለግል ኮማንድ ፖስት ሊመሰርቱ ነው።ይህ ኮማንድ ፖስታችው እኮ ስንቱን አስቀና ሆሆሆ…ወያኔ ጠላቶቼ የሚላቸው ሁለት ሃገራት እንኳን እንዲህ ብለው ይቅርና እንዲሁም በነጻ ወንጀል ለማሸከም ኣይቦዝንም ቢሆንም ከጀርባ ያለውንም የፖለቲካ መነባነብ ሰከን ብሎ ማዳመጥ ይበጃል ወዳጆቼ። በአንድ ጉዳይ የፈዘዘ ደንዝዞ ይቀራል። ነቃ እንበል !! እንብሰል !! አንዘናጋ !! ይህን ስል ደግሞ ወዲ ሳልሳዊ ሻእቢያና ወያኔ የተጠና ፖለቲካ ያሴራሉ ብሏል ብለህ መርዝ ምላስህን ዘርጋው አሉ:: #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment