Saturday, November 19, 2016

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ድርቅና ኮሌራ የዜጎችን ኑሮ እየጎዱ መሆኑን ኦብነግ አስታወቀ


በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ድርቅና ኮሌራ የዜጎችን ኑሮ እየጎዱ መሆኑን ጠቅሶ ባለፉት አራት ቀናት ከሰላሣ ሰዎች በላይ መሞታቸውን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) አስታውቋል።
በክልሉ ከአንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች በድርቅ ምክንያት ለምግብ እጥረት በመጋለጣቸው ለበርካታ ወራት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ሲደረግላቸው መቆየታቸውን የብሔራዊ የአደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ አመልክተዋል፡፡
በአካባቢው የዳይር ዝናብ መስተጓጎሉን ኮሚሺነሩ ገልፀዋል።
በክልሉ ተከስቶ የቆየውን የኮሌራ በሽታ ለመቆጣጠርም የጤና ጥበቃ ሠራተኞች የተሣካ ሥራ ማከናወናቸውን አቶ ምትኩ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ከተለያዩ አካላት የተውጣጣ ግብረ ኃይል ከነገ ጀምሮ በመላ ሃገሪቱ የድርቁን ሁኔታ እንዲገመግም እንደሚያሠማራ አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment