Monday, August 8, 2016

በገዱና ብአዴኖች ላይ የተከፈተ ዘመቻ


Gedu-Andargachew
አንድ ጎንደር ተወልጄ አደኩ ያለ ግለሰብ፣ የሕወሃት ካድሬ የጻፈውን፣ “የፖለቲክ ኤሊኖ በኢሕአዴግ” በም፣ኢል ረእስ ስር የጻፈውን አሰልች 13 ገጽ ጽሁፍ ላይ ላይ ገረፍ አደረኩት። ጽሁፉ አንድና አንድ አላም ብቻ ነው ያለው። በብአዴን ላይ ጦርነት ማወጅና በተለይም የክልሉ አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ እርምጃ ማስወሰድ።እናንተን እንዳይሰለአችሁ የተወሰኑት እንደሚከተለው ቆረጥ አደርጌ ላካፍላችሁ።
ይህ ጽሁፍ የተጻፈው ከጎንደር ሰልፍ በኋል ከባህር ዳር ሰልፍ በፊት ነው።
“በቅርቡ በሰሜን ጎንደር ያጋጠመ ግርግር መሰረቱ ወንጀለኞች ይያዙ አይያዙ ከሚል የመነጨ አይደለም። የችግሩ ምንጭ በብአዴን ውስጥ እያቆጠቆጠ ብቻ ሳይሆን እየለመለመና እያበበ ከመጣው የክራይ ሰብሳቢነት ዝቅጠት አደጋ ለመሆኑ የፖለቲካ ትምህርትም ሆነ ፍልስፍና የሚጠይቅ አይደለም። ይህ የአጥፊነት መንገድ ደግሞ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ መሆኑ ነው። አቶ ገዱ በምርጫ 1997 ዓ/ም በባህርዳር አንድ እራት ቤት አብረው ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዱ የሞያ ባልደረባ ስለነበር እንዳወራኝ ያኔ ኢህአዴግ ለምን በብዙ ቦታ ተሸነፈ የሚል ሃሳብ ተነስቶ በሚወያዩበት ወቅት አቶ ገዱ ‘’ጉዳዩ በአንድ ወይም በሌላ ምርጫ ጣብያ መሸነፍ ሳይሆን ያጋጠመው የጠቅላላ ስርዓት ውድቀት ነው።’’
“በወቅቱ እሳቸው የተጠቀሙት ቃል እንግሊዝኛ ስለነበረ ‘’system failer’’ ነው ብለው ሲናገሩ ሰምቶ ደንግጦ በተገናኘን ግዜ ሲያነሳልኝ ለምን እንደዚህ አሉ ብለን በወቅቱ ስንገመግም የሰውየው የአቅም ውስንነት እንደሆነ ነበር የፈረጅነው። ሰውየው ከዚህ ችግር የሚያመልጡ ባይሆኑም ዋና መነሻው ግን ከፖለቲካ አቋማቸው በማፈንግጥ ወደ ክራይ ሰብሳቢነት መንገድ መግባት መጀመራቸው ነበር። ከዛ በኋላ ‘’መንግስት የለም’’ ብለው ያመኑ ሰው ድርጅቱ ወይም ራሳቸው ከኃላፊነታቸው ይነሳሉ ብለን ስንጠብቅ ይባስ ብሎ ኃላፊነታቸው እያጠናከሩ መምጣታቸው አስገራሚ ነበር።አቶ ገዱ ወደ ክራይ ሰብሳቢነት መንገድ ከገቡ በኋላ አንደኛው የክራይ
መሰብሰብያ ምንጭ አድርገው መጠቀም የፈለጉት የሰሜን ጎንደር ሰፋፊ መሬቶችን ሲሆን በተለያየ ዋጋ ሲሸነሽኑ ከቆዩ በኋላ በዞኑ ያለ የብአዴን አባል እየተቃወመ እያለ የግብርና ቢሮ ኃላፊነታቸው ተጠቅመው ብአዴን ወደ ልማት እንዲመሩት የሰጣቸው የመሬት አመራርነት እሳቸው ወደ ገበያ አቀረቡትና እንደ ቴሌ ገቢ ገንዘብ ማለብ ብቻ ሆነ።ህዝቡ ከማማረር አልፎ እስከ ፌደራል መንግስት ድረስ የሰሚ ያለ ብሎ ሰሚ ሲያጣ ተደራጅቶ ወደ ሽፍትነት እስከ መውጣት ሲደርስ እሳቸው ከግብርና ቢሮ ኃላፊነት ወደ ክልሉ ፕሬዝዳንትነት ተሸጋግረው ነበር። በዚህ ወቅት ከህዝቡ አልፎ አንዳንድ የብአዴን አመራሮችም ጭምር ስለ ጉዳዩ ማንሳት ሲጀምሩ አቶ
ገዱ ከጎናቸው የሚሰለፍ ሰራዊት ማብዛት እንዳለባቸው አሰቡና ከዞኑ አስተዳዳሪ የነበሩ አቶ ግዛት ጀምሮ በዞኑ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮችን በአንድ ለአምስት የኢህአዴግ የህዝብ አደረጃጀት ውድቀት እንደ ተሞክሮ በመውሰድ በአንድ ለሺህ አደረጃጀት የተሳካ የክራይ ሰብሳቢነት የጥፋት ሰራዊት በማደራጀት ለአላማቸው መሳካት የሚያስችሉ መረሀ ግብር በመንደፍ መንቀሳቀስ ጀመሩ።”
‘’የወልቃይት ህዝብ አማራነቱ ለትግሬዎች የሸጡት እነ አዲሱ ለገሰ ናቸውና ማስመለስ አለብን’’ የሚል ስልት ቀይሶ የአማራ ተቆርቋሪነት ስሜታቸው ከፍተኛ እንደሆነ፣ ለህዝቡም ለመዋቅሩም
ማስረጽ ነው። ለዚህም ከወልቃይት ከባቢ የአስተዳደር በደል ደረሰብኝ የሚልና ጎንደር የሚሰባሰብ ሰው ሁሉ ጥሩ አቀባበል ከማድረግ አልፎ ለጎንደር ህዝብ ሩቅ የሆነው የመኖርያ ቤትና የእርሻ ቦታ መስጠት፣ቀጥሎ እርስበርሳቸው እንዲሰባስቡ ማድረግ፣ቀጥሎ ሰዎች እየመረጡ አንድ በአንድ ማነጋገር፣ቀጥሎ ኮሚቴ በማደራጀት ጥያቄ እንዲያቀርቡ ማድረግ፣ቀጥሎ ጥያቄ ስለቀረበልን አዳመጥናቸው ማለት ፣ ቀጥሎ እነ እገሌ የተባሉ የቅማንት ኮሚቴ ጎንደርን እየበጠበጡ ያሉት መቀሌ ቤት ተሰጥቷቸው ከህዋሃት መመርያ እየተቀበሉ አንደሆነ በቂ መረጃ ደርሶናል በማለት ወሬው በክልሉ ሁሉም ቦታ እንዲዳረስ በማድረግ የወልቃይት ኮሚቴ ብለው ያደራጇቸውን
ሰዎች በግልጽ ወደ ቢሮ እየጠሩ ቀን በቀን መሰብሰብና አደረጃጀቱ ማስፋት ዋናው የዞኑ የልማት እቅድ ሆኖ ቀጠለ። ይህ ሁኔታ ያልጣማቸው አንዳንድ የብአዴን አመራሮች ሃሳብ ማንሳት ሲጀምሩ በአሽሙርና በቀጥታ የህዋሃት ተለጣፊዎች በማለት እንዲሸማቀቁ ማድረግ ዋናው ስልታቸው በማድረግ አመራሩም አብዛኛው ዝምታ እንዲመርጥና በግዜ ሂደት ንፋሱ እያየ እንዲከተላቸው
በተጠባባቂነት ማስቀመጥ የቻሉ ሲሆን ጥቂቱ አሁን ከጎናቸው እንዲሰለፍ ሌላው የቀረው ጥቂት እየተቀለደበትም ቢሆን መቃወሙ የቀጠለ ሲሆን የመጨረሻው ጥቂት ኃይል ደግሞ ዘሩ ተቆጥሮ ‘’የክፉ ቀን መርተህ እዚህ ካደረስከን እናመሰግናለን የክብር እንግዳ ብቻ ስለሆንክ አፍክን ዝጋ’’ ይህም እንየሁኔታው ከዛ በላይ ሊሄድ ይላል የተባለ ሆኖ እየቀጠለላቹ ነው።”
“የፌደራል መንግስት ዝም ብሎ ላያየን ይችላል በሚል ግምት ስለያዙ የጎንደር ህዝብ በተለይ የቆላው አከባቢ ህዝብ ከመሳርያ ጋር ያለው ቁርኝት እና ይህ ህዝብ ማሳመን ከቻሉ ያለው የጀግንነት ታሪክ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከጥቂቶች በስተቀር የአለም መንግስታት
ሁሉ በአንድ ድምጽ እያወገዘው እና ለመከላከል የአብረን እንስራ ጥሪ እያቀረቡ ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ምርጫ 2007 ዓ/ም በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ የጦር መሳርያ ቁጥጥር እንዲደረግ እየተሯሯጠ በነበረበት ሁኔታ የጦር መሳርያ ፍቃድ ስለምንሰጥ የሰሜን ጎንደር ህዝብ ተሎ እያስመዘገብክ መሳርያ ታጠቅ የሚል አዋጅ በማስነገር ጎንደርን ወደ ጦር መሳርያ ገበያ ማእከል ተቀየረች። በመሆኑም ከደቡብ ሱዳን፣ከሰሜን ሱዳን፣ከሞያሌ፣ ከቶጎ ውጫሌ፣ከአፋር እንዲሁም ከሌሎች አከባቢዎች የተለያዩ የጦር መሳርያዎች በገፍ ወደ ጎንደር መትመም ጀመሩ ፣ዋጋው ጣርያ ነካ። ይህንን ሁኔታ ሌላ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ የተገነዘቡ እነግዛትና የዞኑ ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች የመንግስትን መሳርያ ከግምጃቤት እያወጡ ገበያ ላይ አቅርበዋል። ይህ ሁኔታ እኔ ወላጆቼ ለመጠየቅ ጎንደር ህጄ በአካል ያየሁት ነው ። በዛን ወቅት በቤተሰቦቼና ህዝቡ በጠቅላላ የነበረው ስሜት ‘’መንግስት ከምርጫው በኋላ ከፍተኛ ትርስም እንደሚኖር ስላወቀ ነው ይህንን እያለ ያለው’’ የሚል ከፍተኛ ሽብር ውስጥ የገባበት ሁኔታ ነበር ። የኔም ቤተሰብ ከምርጫ
በኋላ ከተማው በዝርፍያ ሊተራመስ ስለሚችል ቤታችን ለመጠበቅ መሳርያ ካልገዛህልን ብለዉኝ እስከመጣላት ደርሰን ነበር።”
“ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ገዱ ዲያስፖራውን ለማሳመን በሚል ውጭ አገር ሲመላለሱ መክረማቸውና እዛ በሄዱ ግዜ እነ እገሌን አገኙ እየተባለ የሚወራው በራሴ ወይም እኔ በማምነው ሰው ያረጋገጥኩት ስላልሆነ በዚህ ጽሁፍ እንዳለ ላቀርበው አልፈለግኩም።ሆኖም በበቂ የፖለቲካ ጤንነት እንደሌሉ ብቻ ሳይሆን በግላጭ ፀረ-ኢህአዴግ እንቅስቃሴ እያደረጉ ስለመሆናቸው ግን
ከእውነት በላይ ሆኖ እያየነው እንገናኛለን።”
“በቅርቡ በቴሌቪዥን ተፈላጊ ተብሎ ስሙ የተጠቀሰው ደጀነ ማሩ የተባለ ሰው ሲሆን ከዚህ በፊት በመልካም አስተዳደር ተማሮ ኤርትራ ካለው ፀረ-ሰላም ጋር እስከመደዋወል ደርሶ እንደነበር አንድ የፌደራል ፖሊስ ዘመዴ ነግሮኝ ነበር። ለእስር መፈለግያ ትእዛዝ ሲወጣለት እነ ገዱና ግዛት መልካም አጋጣሚ አግኝተው ለመታረቅና እንዳይያዝ ከለላ እንዲያገኝ በማሰብ የሁለቱ ጠገዴ የድንበር ክርክር ‘’ለሽምግልና ህዝቡ መረጠው’’ በሚል የኮሚቴ አባል እንዲሆን አደረጉት ብቻ ሳይሆን ሰሞኑን መንግስት አፋልጉኝ ሲል ሰውየው ከነ ሙሉ ትጥቁ ጎንደር ከተማ ሆኖ
ታጣቂዎችን አደራጅቶ በግጭቱና በጥፋቱ ዋና አዝማች እንደነበር በአካል የሚያውቀው የክልሉ ልዩ ኃይል አመራር አረጋግጦልኛል።”
“የመንግስት ኃላፊነታቸው በመጠቀም በጎንደር ለተካሄደ ህገ-ወጥ ሰልፍ ቢያምንበትም ባያምንበትም በኮሚኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ አመካኝነት ‘’ህገ-ወጥ ሰልፍ ስለተካሄደ ይህንን ፀረ-ህገ መንግስት ስራ የሰሩ ወደ ህግ እናቀርባለን ‘’ ሳይሆን ‘’ሰልፉ ህገ-ወጥ ቢሆኑም ጥያቄያቹ ትክክል ስለሆነ ተቀብለነዋል።’’ ብለው መግለጫ ሰጡ ።ልብ በሉ ትክክል ተብሎ በክልሉ ሙገሳ የተቸረውና በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተላለፈለት መግለጫው ‘’ወንጀለኛ መታሰር የለበትም ይፈታ፣ ትግሬ ከተከዜ ወዲህ አገር የለውም።’’የሚሉትን እና ሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ አንድነት መፎክሮችን ላነገበ ህገ-ወጥ ሰልፍ ነው”

No comments:

Post a Comment