ሕወሃት የተወሰነ መሬት ከወለጋና እጅግ በጣም ሰፊ ግዛት ከጎጃም በመዉሰድ እንደ አፋር ክልል ለብቻው የሚቆጣጠረው የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ከጅምሩ በዲዛይን መመስረቱ ይታወቃል። የበጌምድር ግዛት የነበረችዋን ወልቃይት ጠገዴን በሃይል ወደ ትግራይ ቀላቅሏታል።
አሁን የአማራ ክልል በሚባለው ግዛት በስተምራብ የበለጠ የአማራን ክልል በመሸንሸን፣ በበላይነት የሚቆጣጠረው ቅማንት የሚባል ክልል ለመመስረትና ትግራይን ከበኔሻንጉል ለማገናኝት ህወሃት ፍላጎት እንዳለው የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም። በመቀሌ ያደራጃቸዉና ያሰባሰባቸው “ማንነታችን ይከበር፣ የራሳችን ክልል ይኑረ” ብለው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ እንዲያስገቡ ሕወሃት አደረገ። የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ የአማራው ክልል የበለጠ እንዲሸነሸን ወሰነ። (ያወ በሕወሃት የሚታዘዝ በመሆኑ) በዚህ ጊዜ ሕወሃት ባሰማራቸው ሰዎች አነሳሽነት በአካባቢው የተወሰኑ ግጭቶች ተፈጠሩ። አማራዉን እና ቅማንቶችን ለማጣላት፣ ለማጫረስ ብዙ ተዶለተ። (ኦሮሞዎችን እና አማራዎችን ሲያጣሉና ሲያቃቅሩ እንደነበረው) ደግነቱ የአገር ሽማግሌዎች የሕወሃትን መርዝ አመከኑት።
በዚህ ወቅት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሕወሃት አሽከር ከፋፋዮችን ሰይጣኖች ነበር ያሏቸው። በወቅቱ
“ቅማንትና እና አማራን ለመከፋፈል መሞከር አንድ ሰው ለሁለት ከፍሎ ሕይወት ይኑርህ ማለት ነው። እነዚህ ህዝቦች ለየብቻ የሚሆን ነገር የላቸውም። እጣ ፋንታቸው አንድ ላይ ነው። እጣ ፋንታቸው ተፋቅሮ መኖር ነው። ተደጋግፎ መኖር ነው። ተከባብሮ መኖር ነው። ይሄንን ለመለያየት መሞከር ሰይጣናዊ ከመባል በስተቀር ሌላ ሊባል አይችልም”
ነበር ያሉት። ያኔ ተነስቶ የነበረዉን ቀዉስ በማርገብ አንጻር አቶ ገዱ የተናገሩት በጣም አስደናቂ አባባል ነበር። አሁን በጎንደር እና ጎጃም ወታደር እየላኩ በሃይልና በጉልበት የሕዝቡን ጥያቄ ለመደፍጠጥ እየዋተሩ ያሉ የሕወሃት መሪዎች አቶ ገዱን እንዲሰሙ የአቶ ገዱን ንግግር ጋብዣቸዋለሁ፡
አቶ ገዱ ችግሮች ከማህበረሰቡ ጋር በመወያየትና በመመካከር ካልተፈቱ፣ በደህነነት፣ በፖሊስና በመከላከያ ሃይል የሚፈታ ነገር እንደማይኖር ነበር በግልጽ ያስቀመጡት።
የጎንደር እና የጎጃም ህዝብ ቁጭ ብሎ በማናገር፣ በማወያየት፣ ሕዝቡን በማክበርና የሕዝቡን ጥያቄ በመመለስ እንጅ፣ በሃይል፣ በጉልበት የሚሆን ነገር አይኖርም። አቶ ገዱ ትክክል ናቸው። ይሄንን አዘዞና ብር ሸለቆ ያለው የመከላከያ ሰራዊት አውቆታል። አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ባህር ዳር ተጭነው የመጡና ከትግራይ በጋንይት በኩል እያመሩ ያሉትም በቅር የሚያዩት ይሆናል።
ወያኔዎች በየሜዲያችሁ አቶ ገዱ ላይ ዛቻና ማስፈራራት ከምታደረጉ፣ እኝህ ሰው ብታዳምጡ ኖሮ ጥሩ ለናንተው ጥሩ ይሆንላችሁ ነበር።
No comments:
Post a Comment