Tuesday, August 16, 2016

ጥያቄወቻችን ግልፅ ናቸው” ከደብረ ማርቆስ

13962724_167168567041318_7615931692195659232_n
“ጥያቄወቻችን ግልፅ ናቸው”
እንደ አማራነታችን
‪#ዋናው ጥያቄያችን ይህ ነው!!!!
እንደ ማርቆሴነታችን ደግሞ
1. ዛሬ ከሰሃት በኋላ ይፈታሉ የተባሉ ወንድሞቻችን ይፈቱ
2ኛ. የከተማው ይሁን የዞኑ አስተዳደር ተወካዮችን ልኮ ሳይሆን ራሱ ወደታች ወርዶ ሁሉንም ህብረተሰብ ያወያይ
የቀበሌ ካድሬና የካቢኔ አባል ብቻ እየሰበሰቡ ማወያየት ውጤት አያመጣም!
3ኛ.በከተማችን ካሉ ታክሲዎች እና በትራንስፓርት አገልግሎት የተሰማሩ ባለሃብቶችና ሰራተኞችን ሰብስቦ ያለባቸውን ችግር ትራንስፓርት ፅ/ቤቱ ይፍታ!
4ኛ. በነጋዴው ህብረተሰብ ላይ የሚጣለውን ከመጠን ያለፈና በትክክለኛ መንገድ ያልተጠና ግብር ብዙ ነጋዴዎችን ሀገር ለቀው እንዲሰደዱ ምክንያት እየሆነ ስለሆነ መፍትሄ ከሚመለከተው አካል መፍትሄ እንፈልጋለን!
5ኛ.በፓለቲካ አቋማቸው ብቻ ተመርጠው በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ያለ ሙያና ብቃታቸው የተቀመጡ አመራሮችና ሃላፊዎች ተነስተው ሙያና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎ ይተኩ!
በመጨረሻ
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተገኛችሁ የተባሉና በአቃጣሪዎች ተጠቁመው ከየ ቤታቸው ታፍሰው እስር ቤት የሚገኙ ውንድሞቻችን ዛሬ ካልተፈቱ ከነገ ዕሮብ ነሐሴ 11 ጀምሮ ተቃውሞው ከቤት ባለመውጣት ይቀጥላል!!
በዚህ አጋጣሚ
– የደብረማርቆስ የንግድ ማህበረሰብ እያሳያችሁ ላላችሁት ቁርጠኝነት ታሪክ ሲያመሰግናችሁ ይኖራል!
-ታስረን የነበርነውን ያስፈታችሁንና ታስረው የሚገኙትን ለማስፈታት ላይ ታች እያላችሁ የምትገኙ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን!
መብታችን በእጃችን ነው!
ደብረ ማርቆስ ወደ ቀድሞው ታላቅነቷ እንመልሳታለን!!
‪#‎ሼር_ማድረግ_አትፍሩ‬

No comments:

Post a Comment