ባለፈው ሳምንት ጌታቸው ረዳ ከአልጃዚራ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ጋር ተጋፍጦ ነበር። አንድ ጥያቄ ቀረበለት።”በራሳችሁ የምትተማማኑ ከሆነ ለምን የተባበሩት መንግስታት ታዛቢዎች እንዳይገቡ ከለከላችሁ?”
ምኒስቴር ጌታቸውም። “የተባበሩት መንግስታት አያስፈልገንም። እኛው ራሳችን ከህዝቡ ጋር እንነጋገራለን።” ሲል ነበር የድፍረት መልስ የሰጠው።
ይህ የትእቢት መልስ ለጋዜጠናዋ እንግዳ ቢሆንም፣ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ግልጽ ነበር። እነሆ ከህዝብ ጋር ንግግር መጀመራቸውን እያሳዩን ነው። እንደ ፋሺሽት ጣልያን በከባድ መሳርያ ሕዝብን ለመደብደብ ቆርጠው መነሳታቸውን ተመልከቱ።
በምክትል ጠቅላይ ምንስቴርነት ማእረግ ሃገሪቱን የጠቆጣጠሩት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ማርያም በዛሬው እለት በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አንድ የጦር አዋጅ አስነብበውናል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ተታወጀ ጦርነት። የጦርነት መግለጫው እንዲህ ይነበባል፤
“ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን የሀገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ ከመቸውም ጊዜ በላይ በነቃ እና በተጠናከረ ሁኔታ በመንቀሳቀስ፤ በቅርቡ በሃገራችን የተከሰቱ አመፆችን ስልታዊ በሆነ መልኩ ሥርዓት በማስያዝ ላይ ይገኛል።በየክልሉ የሚነሡ ረብሻዎችን ሰበብ በማድረግ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመካሄድ ላይ ይገኛል። በተለይም ብጥብጡ ከበረታባቸው አካባቢዎች የጎንደር ነውጥ በጉልህ የሚጠቀስ ሲሆን ሠራዊታችን ከነውጠኞች ጋር ያደረገውን ፍልሚያ በጀግንነት እየተወጣ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አመፅ ፈጣሪ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት የጦር መሣርያ የማስፈታቱ ሂደት የመንግሥት የቅርብ የቤት ሥራ ይሆናል። እንደዚህ ዓይነት ሥርዓት አልበኝነትን የማክሸፉ ሂደት በተጠናከረ ሁኔታ የሚቀጥል ነው የሚሆነው። ድል ለመከላከያ ሠራዊታችን!”
የዚህ “አዋጅ” ትርጉም ግልጽ ነው። የሕዝበን ጥያቄ በማሳርያ ለመስበር ከመቸውም ጊዜ በላይ መነሳታቸውን ነው ደብረጽዮን ያሳወቁን። በአጭሩ ለአራትና አምስት ሰዎች ደህንነት ሲባል በመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ጦርነት ለመግጠም የተሰጠ መግለጫ ነው።
ከዚህ ቀደም ውስጥ ለውስጥ ይናገሩት የነበረውን ምስጢራቸውን አሁን በይፋ በአደባባይ መናገር መፈለጋቸው አንድ ከበድ ያለ ችግር ውስጥ እንዳሉ ያሳየናል። እንዲህ አይነት ድፍረት የተሞላበት ንግግር በአደባባይ ወጥተው የመናገራቸው ምክንያትም ምስጢር አይደለም። የህወሃት የውስጥ ምስጢሮች ሁሉ በራሳቸው ሰዎች እየሾለኩ ወደ መገናኛ ብዙሃን መድረሳቸው ይመስላል ለእንዲህ አይነት ንቀት እና ድፍረት ያበቃቸው።
የፌስቡኩ ሚንስቴር ቴድሮስ አድሃኖምም ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የጦር አዋጅ አሰምቶን ነበር፤
“..ይህንን ምክንያት በማድረግ የሚነሡ ረብሻዎችን መንግሥት ለመታገስ የሚቸገር በመሆኑ ሕግ የማስከበር ኃላፊነቶቹን በመወጣት ላይ ይገኛል። ነፍጠኛ አመለካከት ባላቸው ኃይሎች የሚነሣ አመጽ ምንጊዜም ቢሆን መድረሻው ከሁለትና ሦስት ቀን ያልበለጠ ግርግርና ረብሻ ነው። … በመሆኑም መንግሥታችን ነፍጠኝነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ከሀገሪቱ ለማጥፋት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ልብ በሉ ሕዝባዊ አመጹ እየተካሄደ ያለው በመላው ኢትዮጵያ ነው። እነዚህ የህወሃት ምኒስትሮች እየነገሩን ያለው ደግሞ ይህንን ህዝብ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ እንደመስሰዋለን ነው።
እነዚህን ጠባቦች እንደ መንግስት ለሚመለከቱት ሁሉ ጄኔራል ፃድቃን ገብረተንሳይ መልስ የሰጠ ይመስለኛል። በቅርቡ በኢንተርነት በለቀቀው ጽሁፍ ጄኔራል ፃድቃን እንዲህ ብሎናል።
… በርከት ባሉ የትግራይ ተወላጆች የሚነሳ አንድ ጥያቄ አለ። ይኸውም አሁን ባለው መንግስት ላይ ያለንን “የበላይነት” ካጣን ጠቅላላ መብቶቻችን አንድናጣ መልሰን እንድንጨቆን አድልዎ እንዲፈፀምብን ቢደረግስ ምን ዋስትና አለን? የሚል ነው። ዋስትናችን በትግላችን ያገኘነው አሁንም ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሆነን እየታገልን የምንጠብቀው ሕገ-መንግስታችን ያለምንም ማቅማማት ተግባራዊ ማድረግ ነው።…
ሕገ-መንግስታችን የሚሉት ስልጣን ለማለት ነው። የስልጣን ወይም ሞት ምስጢሩም ይህ ነው።
በሕዝብ ላይ ጦርነቱን ጀምረውታል። ውጤቱን ደግሞ በቅርብ የምናየው ይሆናል። ከህዝባቸው ጋር ውግያ ገጥመው የዘለቁ አንባገነኖች ከተፈጠሩ እነዚህ የመጀመርያዎቹ ይሆናሉ።
No comments:
Post a Comment