Tuesday, August 16, 2016

በሚኒስቴር ደረጃ ስራዬ ብላችሁ ቢሮ ከፍታችሁ ታሰድቡናላችሁ። – የደብረማርቆስ ህዝብ


የዛሬዉ የደብረማርቆስ ህዝብ ከዞኑ እና ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር ባደረገው ዉይይት ህዝቡ በከፍተኛ ወኔ ሲያሰማቸዉ የነበሩ ሀሳቦች
~ወልቃይት በማያሻማ ሁኔት የአማራ ነው እንኳን ወልቃይት በወሎ የተወሰዱትንም እናስመልሳለን
~በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የታሰሩት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ
~ልጆቻችንን በአጋዚ ጦር አስደበደባችሗቸው
~ በየቀበሌው ያሉት ውሾቻችሁ ቤታችንን እያንኳኩ አላስቀምጥ ብለውን ነበር/እንዳትወጡ እያሉ/ እነዚህ በኛ መካከል የሚኖሩ ጠላቶቻችን ናቸው ።
~እኛን ሰብስባችሁ ከማነጋገር ይልቅ ጦር እያደራጃችሁ ነበር፣ በዚህም ተጠያቂው አንተ ነህ/ አቶ ምግባሩን/
~ሰልፉን የጠሩት ህገወጦች ናቸው አትበሉ። የሰልፉ ባለቤቶች እኛ ነን። እራሳችን የጠራነው ሰልፍ ሆኖ ሳለ በሻዕቢያ ታመካኛላችሁ። ለሀገር ለወገን የሚጠቅመው ብንደማመጥ ነበር፣ እናንተ ግን ህዉሓት የጫነቻችሁን ዘፈን መጥታችሁ ትዘፍናላችሁ።
በሚኒስቴር ደረጃ ስራዬ ብላችሁ ቢሮ ከፍታችሁ ታሰድቡናላችሁ።
ስንት ፋብሪካ አሳይታችሁ እንደነሳችሁን እና ስንት ጊዜ ልጆቻችንን እንዳሳቀቃችሁ የአብማዋ ማርያም ትመስክር…….
ሌላም ሌላም ብለዋል።
ባለስልጣናቱ የተባለውን ከሰሙ በኋላ የወልቃይት ጉዳይ አንዳንድ የፌዴራል ሀላፊዎች እንደሚሉት ያለቀ ጉዳይ ሳይሆን ህግ የያዘው እና አስቸኳይ ዉሳኔ የሚሻ እንደሆነ ጠቁመዋል።

No comments:

Post a Comment