Thursday, August 25, 2016

በመላው ኢትዮጵያ ከባድ ተቃውሞ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።


በመላው ኢትዮጵያ ከባድ ተቃውሞ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።Minilik Salsawi
ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲጠባበቅ መሬት ላይ የወረደ ስራ እየተሰራ ነው።
በመላው ሃገራቸውን በተለይ በከተሞች ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ይደረጋል በማለት በሃገር ውስጥ የሚገኙ የለውጥ ሃይሎች ኣስታውቀዋል፤ በሕዝቡ መሃል ኣስፈላጊ የሆኑ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ሕዝቡ ራሱን እያደራጀ በመተባበር በንቃት በተጠንቀቅ እንዲጠባበቅ ላልሰሙ ሁሉ እንዲያሰሙ የለውጥ ሃይሎቹ መልእክት ኣስተላልፈዋል።
የሃገሪቱን የማፊያ መንግስት በበላይነት የሚመራው ሕወሓት መሆኑ እሙን ነው፥ ሕወሓት ከስሙ ጀምሮ እንደሚያሳየን ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን የማይተኛ ድርጅት ነው። ከሕወሓት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን አሊያም የሕዝብ ስልጣን መጠበቅ ከእባብ የእርግብ እንቁላል እንደመጠበቅ ነው። ይህ ድርጅት ከበረሃ ጀምሮ ይዞ የመጣውን ጸረ እትዮጵያ አቋሙን ለመተግበር ሃገርን እና ሕዝብን አደጋ ውስጥ ጥሎ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል በመስራት ላይ ነው፥አመራሮቹም ቢሆኑ የሚሰሩት ግፍ ዘረፋ እና ይቅር የማይባል ተንኮል ሕዝቡን ለድህነት ሃገርን ለውርደት ዳርጓል፥ማወቅ ያለብን እነዚህን ተኩላዎች ማስወገድ ብቻ ነው በሚገባቸው ቋንቋ ልንነግራቸው ይገባል። ሕወሓቶችን በምናስወግድበት ላይ ሁሉ ልንረባረብ ይገባል።

No comments:

Post a Comment