Sunday, August 21, 2016

የአዲስ አበባውን ሰልፍ ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲ ኣባላት አፈና ተጀመረ።


ወያኔ ምን ያህል ቦቅቧቃ እንደሆነ በኣዲስ ኣበባ የሰልፍ ጥሪ ላይ ኣየነው እንደ ኦሮሚያና ኣማራ ክልሎች ሰልፉ ኣደራጅ ቢኖረው ደሞ ትልቅ ስራ ይሰራ ነበር። ይህv ሰልፍ ጠሪ ብቻ ነው ያለው ድክመቶች በቀጣይነት ይታረማሉ።
የሰልፉ ኣስተባባሪዎች የተቀናጀ የመረጃ ስራ ኣለመስራታቸው ሰልፍ ጠሪ እንጂ ኣስተባባሪ እንዳሌለው ያሳያል፤ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ኣዲስ ኣበባ ፖሊሶች ሰልፍ ያደረጉ እስኪመስል ድረስ በፌዴራል ፖሊሶች ከመንደር እስከ መንገድ ተጥለቅልቋል፤
ከአርብ እለት ጀምሮ በኣፈሳ በማስፈራርያ በመግለጫ ዛቻ ወያኔ ምን ያህል ፈሪ እንደሆነች በተርበተበተ ስልጣን ላይ ኣዘምማ እያዘገመች እንደሆነ በተግባር ኣይተነዋል፤ በቀጣይነት በዚህ ጥሪ ሰበብ በኣዲስ ኣበባ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲ ኣባላትን ማፈን እና ማሰር ይቀጥላል፤ በኣዲስ ኣበባ ሰዎች ላይ ፈጥኖ መፍረድ የፖለቲካ ትግልን ኣለማወቅ ነው፤ ትግሉ ይቀጥላል። ድል የሰፊው ሕዝብ ነው። 
ስንታየሁ ቸኮል
ስንታየሁ ቸኮል የተባለ ጀግና ወጣት ታስሮ ከታሰረ ከወራት በሁላ ሲታገል ቆይቶ በድጋሚ ታስሯል። ከመታሰሩ በፊት በፌስቡኩ ፅፎት የነበረው እጅግ የሚገርም ነው እነሆ
“ለነፃነት መታሰር ክብራችን እንጂ ውርደት አይደለም፡፡ ይህ የመጨረሻ ቃሌ ሊሆን ይችላል፡፡ የፈራ ይመለስ እንዳለው ትንታግ ማለት ነው፡፡ የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ተከተሎ እረፍት የነሳው ስርዓት በከተማው ውጥረቱ አደገኛ አድርጎታል፡፡ በዚህም ከቄራ አካባቢ አቶ ተፈራ ተስፋዬ በደህንነት ታፍኖ ሄዷል፡፡ አቶ ተፈራ ተስፋዬ በ97 ቃሊቲ እስር ቤት ታስሮ የወጣ ሲሆን የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የቅርብ ወዳጅና ጠያቂ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ አሁን በዚህ ሰዓት ሶስት የደህንነት አባሎች በእኔ መኖሪያ ቤት እንደመጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስፍራው ሲያጡኝ እስካሁንም በአካባቢው ቆመው ይገኛሉ፡፡ ቅጥረኛ ካድሬ ጨምሮ መውጫ መግቢያ ላይ አድፍጦ አንደሚገኝ ከቅርብ ሰዎች መረጃ ደርሶኛል፡፡ የህወሓት መንግስት በመጣበት ሕዝባዊ እምቢተኝነት መቀበሪያው ደርሶ በምጥ ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሄን ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለማቀዝቀዝ የለውጥ ሃይሉን በመግደልና በማሰር ለማብረድ እየተሯሯጠ መሆኑ ያሳያል፡፡ አንድ ነገር ሊረዱ ይገባል፡፡ ማንም ሰው ሀገር ተቀምቶ በቀኝ ገዢ ብትር አንገት ደፍቶ መኖር አይቻልም፡፡ ዛሬ ጥቂቶች ብቻ የሚቦርቁበት ሀገር አብቅቶለታል፡፡ ዛሬ በፍርሃፍ ድሪቶ ተከናንቦ ራሱን ለባርነት አሳልፎ ጊዜውን የሚፈጅ ወጣት እንግዲህ የለም፡፡ ዛሬ ከልጅ እስከ አዋቂው ሁሉም ለክብሩ ተነስቷል፡፡ ዛሬ የነጻነት ትግሉ ሞት የማይፈራ እስር የማያንበረክከው ጀግና ትውልድ ተፈጥሯል፡፡ ይሄን እያየን ከፊታችን የሚታየው ድል እያጣጣምን ባለንበት ሰዓት የቱንም አይነት ሃይል ቢበዛ ምንም ጫና ቢደረግ ወደኀላ በማይቀለበስበት ደረጃ የነጻነት ትግሉ አድጓል፡፡
የአዲስ ልጅ አደባባዩን ተጠቀምበት
ድል ለጭቁን ሕዝብ!! ” ስንታየሁ ቸኮል

No comments:

Post a Comment