Friday, August 12, 2016

ኣፈናና ዛቻ ያልበገራቸው የወሎ ወጣቶች ተጠናክረዋል።ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።


ኣፈናና ዛቻ ያልበገራቸው የወሎ ወጣቶች ተጠናክረዋል። በደሴና ዙሪያዋ ያሉ ወጣቶችን የማፈኑ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል። የደሴ ዙሪያ ወጣቶች በተጠናከረ መልኩ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ዝግጅት የተጠናከረ ሲሆን ኣስፈላጊ የሆኑ ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።
ዛሬ ጠዋት ኮምቦልቻ ከተማ የታፈኑ ወጣቶች
1. ዘሪሁን ገሠሠ
2. ጀማል ኡመር
3. ተማም እና ሌሎችም ሥማቸው ያልታወቀ ወጣቶች በገፍ ታፍሠው ተወሥደዋል:: ዘሪሁን ገሠሠ የኮንቦልቻ ነዋሪ ሲሆን የወያኔ መንግሥት በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚያደርሠውን ግፍ በተደጋጋሚ በማጋለጥ ይታወቃል! በዚህ የተነሣ ከዚህ በፊት ታፍኖ ከሁለት ወራት እሥር በኋላ የተለቀቀ ነበር። ዘሪሁን ገሠሠ በደሴና በኮምቦልቻ ከተሞች የሚደረገውን ሠልፍ ያሥተባብራል በሚል ከፍተኛ ማሥፈራራትና ዛቻ ሲደርሥበት እንደቆየ ይታወቃል!
የዘሪሁን ገሠሠ የፍርድ ቤት ማዘዣ ይህን ይመሥላል። የተጠረጠረበት ወንጀል ግን ግልጽ አይደለም!! ያው እንደተለመደው ፍርድ ቤት ቀርቦ ወንጀል ይጋገርለታል ማለት ነው።የደሴ ዙሪያ ወጣቶች በተጠናከረ መልኩ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ዝግጅት የተጠናከረ ሲሆን ኣስፈላጊ የሆኑ ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።
Gashaw Mersha's photo.
Gashaw Mersha's photo.
ወያኔ በወሎ ከተሞች የሚደረገውን ሠልፍ ለማደናቀፍ የዘመቻ እሥር ከጀመረ ሠነባብቷል። አሁን ከመሸ በደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ ሐርቡ ከተማ ውሥጥ ብዛት ያላቸው ወጣቶች እየታፈሡ ነው። በዚህ ሠዓት አብደላ ሙሃመድ የተባለን ወጣት ከቤቱ ይዘውት ሂደዋል!!የደሴ ዙሪያ ወጣቶች በተጠናከረ መልኩ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ዝግጅት የተጠናከረ ሲሆን ኣስፈላጊ የሆኑ ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ። እንግዲህ ሁላችንም ታሥረን እሥክናልቅ ድረሥ ትግሉ ይቀጥላል!

1 comment:

  1. Enter your comment...
    ከዛሬ 4 አመት በፊት ከ ድምፃችን
    ይሰማ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ
    በደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ ገርባ
    ከተማ ላይ መንግስት በወሰደው
    መጠነሰፊ የሃይል እርምጃ
    በመውሰድ የ3 ንፁሃኖች ሂወት
    በመቅጠፍ ለበርካቶች የአካል ጉዳት
    አድርሶ አልፏል፡፡ በርካቶችን ለእስር
    ዳርጎ ብዙዎችን ለስደት ዳርጎ ያለፈ
    ክስተት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
    ይሄው ዛሬ ደግሞ በመጭው
    እሁድ # ኮምቦልቻ ና # ደሴ
    ለሚካሄደው ተቃውሞ ቅስቀሳ
    ያደርጋሉ ያላቸውን ወጣቶች
    እያሳደደ ማሰር ጀምሯል፡፡ ከትላንት
    አመሻሸ ላይ ጀምሮ በተካሄደው
    የእስር ዘመቻ እስካሁን በለን መረጃ
    አንድ ወጣት ተይዞ ወደ
    # ኮምቦልሻ የተወሰደ መሆኑን
    ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
    # AmharaProtest
    # የኮንቦልቻው_የሰደቃና_የ
    አንድለት ፕሮግራም ሲካሄድ
    ከሌሎች አካባቢዎች የሚመጡትን
    ሙስሊሞች ለማገድ እና
    ወደኮምቦልቻ እንዳይገቡ
    ለመከልከል በመሞከር ከሚጢቆሎ
    አለፍ ብለው ጊዜያዊ ኬላ አድርገው
    ነበር፡፡ ጀግኖቹ
    # የገርባ_ሙስሊሞች በጧት
    ተነስተው ጎዞ ጀመሩ፡፡ ሆኖም
    ኮምቦልቻ ከመድረሳቸው በፊት
    ሚጢቆሎላይ ታገዱ፡፡ የጉዞ
    አላማቸውን በማስረዳት ሰላማዊ
    ሰዎች አንደሆኑ ለማስረዳት
    ሞከሩ፡፡ የዜጎችን የመንቀሳቀስ
    መብት እንዲከበርም ጠየቁ፡፡
    ሆኖም ሃይል እዲጨመርና ህዝቡን
    እንዲመለስ ለማድረግ ሞከሩ፡፡
    በዝህ የተበሳጨው ህዝበ ሙስሊም
    ተቃውሞውን በተክቢራ በመግለፅ
    ከመኪናው እየወረደ ጉዞውን
    በእግሩ ጀመረ፡፡ፌደራሎቹም
    ያላቸውን ሃይል ተጠቅመው
    ለማስፈራራት ሞከሩ፡፡ ህዝቡ ግን
    ባዶጅን እስከ አፍንጫው ድረስ
    የታጠቀን ሃይል ተጋፍጦ ድል
    በማድረግ ኪላውን ጥሶ
    ከሚጢቆሎ በከፍተኛ ተክቢራ
    እያሰማ ወደኮምቦልቻ በ እግሩ
    አቀና፡፡ ይህን የህዝቡን ጥንካሬ
    የሚያቁት ወያኔዎች በእሁዱ
    ተቃውሞም ተመሳሳይ ችግር
    ይገጥመናል በሚል ፍራቻ ቅስቀሳ
    ያደርጋሉ ያሏቸውን ወጣቶች
    እያሳደዱ ማሰር ጀምረዋል፡፡
    ወጣቶች በማሰር እና በማሳደድ
    እሚቆም ትግል አይኖርም!!!
    # AmharaProteste
    # Ethio_Muslim_Pr oteste

    ReplyDelete