Wednesday, August 10, 2016

የሕወሓት የጎሳ ፖለቲካ የወለደው የኦሊምፒኩ ምርጥ ቦርጫም ዋናተኛና የአለማችን ቀርፋፋው ዋና ተወዳዳሪ ‪


Image may contain: 2 people , text
 በቅርብ ጊዜ ኣንድ የውጪ ሚዲያ በኬንያ የሚገኙ ስደተኛ ኦሮሞ ወንድሞቻችን ኣትሌቶች ቃለመጠይቅ ኣድርጎ ነበር።አትሌቶቹ ከተናገሩት ውስጥ ለመጥቅስ ያህል ለትግራይ ተወላጆች እንዲያሸንፉ ቦታ እንዲለቁላቸው የፖለቲካ ትእዛዝ ይሰጣቸዋል፥ይህንን ያሉት የኦሮሞ ልጆች በገዛ ኣገራቸው ባይተዋር ሆነው በችሎታቸው ሊሰሩ ባለመቻላቸው ተሰደዋል።
ኦሎምፒክ መንደር ሪኦ2016 ብራዚል ላይ ደግሞ ኣለምን ጉድ ያሰኘ የሕወሓት የጎሳፖለቲካ ውልደት የሙስናና የዝምድና ፍጥረት የሆነ ኣሳፋሪ ተግባር ተፈጽሟል። “አባቱ ዳኛ-ልጁ ዋናተኛ” ይሉሃል ይኼ ነው. . .”እከክልኝ ልዋኝልህ”. . ..የድራፍት ጠርሙስ የመሠለ ዋናተኛ ባለበት ሀገር ነው ያለነው!. . . ሮቤል የዋና ፍቅር ሊኖረው ይችላል. . ,የሀገር ፍቅር ግን የለውም. . .ሀገሩን ቢወድማ የሌላውን ዕድል ገፍቶ…እሱም ውሃው ውስጥ ተደፍቶ አይቀርም ነበር፡፡ለምን ሆነ ስትላቸው ትግሬ ስለሆነ ነው የምትጫጩት ይሉና የራሳቸውን የዘረኝነትና የበታችነት ብሉኮ ሊደርቡብህ ይዳዳቸዋል፤ እውነትን ለመዋጥ ያልፈጠረባቸው ድዊዎች ፦ ሕወሓቶች ።
የስፖርት መረጃ ኣነፍናፊዋ  እንደጻፈችው :- እዚች ሀገር ላይ እንደ ሮቤል ኪሮስ አባትህ የውሃ ዋና ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ከሆነ ለወጣቶች ማበረታቻ በተሰጠው እድል ዋናተኛ ተብለህ ኦሎምፒክ ትሄዳለህ። አባትህም የውሃ ዋና ቡድን “የቡድን መሪ” ሆኖ ይሄዳል። በሀገርህ ሥንት ታሪክ የሰሩ ጀግና ስፖርተኞች እያሉ አንተ መደበኛ ስራህ ስፖርት ያልሆነ ሰው በኦሎምፒክ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘህ ቡድን እንድትመራ ትመረጣለህ። በውድድር ቀን ግን እንዲህ ጉድህ ለአለም ይገለጥና እነ ዴይሊ ሜይል “የኦሊምፒኩ ምርጥ ቦርጫም ዋናተኛ” ብለው ይሳለቁብሃል። ከ59 ተወዳዳሪዎች 59ኛ መውጣትህ መች ከፋን! “ይሄ በእርግጥ እንዴት ነው ለኦለምፒክ ያለፈው” ብለው የአለም ሚዲያዎች ሲጠይቁ መልስ የቸገረን የሀገርህ ሰዎች ግን እጅጉን በሀፍረት ተሸማቀናል።
.
የውሃ ዋና አሰልጣኙን ከሪዮ ኦሊምፒክ ለምን እንዳስቀሩት ሲጠየቁ “ለአንድ ደቂቃ ውድድር አሰልጣኝ ምን ይሰራል?” ብለው በራዲዮ መልስ የሰጡት አባትህ የ100ሜ ውድድርህን 1 ደቂቃ ከ4. 95 ሰከንድ በመጨረስ “የአለማችን ቀርፋፋው ዋና ተወዳዳሪ” በመሆን ሪከርድ መስበርህን ሲሰሙ ኩራት ተሰምቷቸው ይሆን? (ውድድሩን ያሸነፈው አውስትራሊያዊ Kyle Chalmers 47.9 ሰከንድ ነው ያጠናቀቀው

No comments:

Post a Comment