Wednesday, August 24, 2016

በፖሊስ ቀን በሚሊኒየም አዳራሽ የዐማራ ሕዝብ ሲወገዝ ዋለ


በፖሊስ ቀን የዐማራ ሕዝብ ሲወገዝ ዋለ
ትናንት በሚሊኒየም አዳራሽ በተከበረው የፖሊስ ቀን የዐማራ ሕዝብ ላይ መንግሥታዊ ውግዘት ሲተላለፍ መዋሉን ባአሉን ከታደሙ የፌደራል ፖሊስ አባላት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በየቦታው የተከሰተውን የሕዝብ ተጋድሎና ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የሕወሓት አገዛዝ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ እቅድ ተነድፎ እና ፕሮግራም ወጥቶ ነሐሴ 16 ቀን የፖሊስ ቀን ሆኖ ተከብሯል፡፡
የፖሊስ ቀን የተባለውን በዓል ዐማራ ያልሆኑት እና የብአዴን አባሉ የፌደራል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆነው ነጋ ደሬ (ብሔር ኦሮሞ) በዓሉን እንዲከፍት የተደረገ ሲሆን በንግግሩ በዐማራ ክልል ጥቂት ትህምከተኞች በአንድ ብሔር (ትግሬ) ላይ የጀመሩትን ንብረት መውደም የፖሊስ ኃይላችን በመመከቱ ምስጋና ይገበዋል በማለት ተናግረዋል፡፡
ነጋ ደሬ የተባለው (ዐማራ ያልሆነ የብአዴን አባል) የዐማራውን ሕዝብ ትህምከተኛና ተስፋፊ እያለ ያወገዘው አስቀድሞ በፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነሩ ግብርማይ ከበደ (ትግሬ) በተሰጠው ማስፈራሪያ እንደሆነና ዐማራውን በዐማራው ለማሰደብ የታቀደ እንደነበረ ነው ባአሉ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አባለት የገለጹት፡፡
በበዓሉ ላይ ዐማራን ለመጨፍጨፍ ሒደው ለተገደሉ ትግሬ የፌደራል ፖሊሶች ቤተሰብ ገንዘብ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በሚሊኒየም አዳራሽ በተከበረው በዓል የመንግሥት ፍርሀት በግልጽ የታየ ሲሆን ለፌደራል ፖሊስ አባላትም የኮንዶሚኒየም ቤት እንሰጣለን እያሉ ማባበያ ማቅረባቸው ተገልጧል፡፡ በበዓሉ የታደሙ ዐማራ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባለት በቁጭት መዋላቸውን ጭምር ለማወቅ ችለናል፡፡ በዓሉ ላይ የሞባል ስልክና ካሜራ ይዞ መግባት የተከለከለ ነበር፡፡

No comments:

Post a Comment