Wednesday, August 31, 2016

ለኢትዮጵያውያን ምሁራንና ሊቃውንት የፊርማ ማሰባሰቢያ ጥሪ


በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሠተው ጉዳይ ላይ የሕዝባዊ ማስታወቂያ ጥሪ ከአቤቱታ አቀነባባሪ ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ የሰብእና [humanities]ና፣ የማኅበራዊ[social sciences]፣ እንዲሁም የሳይንስ [sciences] ጥናቶች ሊቃውንትና ምሁራን የሆኑት ኢትዮጵያውያን ባገራችን ውስጥ የተፈጠሩት አንገብጋቢ የፖለቲካ፣ የሰብኣዊ መብት፣ የምጣኔ-ሀብትና የማኅበራዊ ኑሮ ከፍተኛ ቀውሶች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ለማድረግ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ አቤቱታ ለማቅረብ፣ ከላይ የተጠቀሰው ኮሚቴ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ኮሚቴው በውጭ የምትኖሩት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትና ምሁራን የሆናችሁ በሙሉ ከዚህ በታች በሚገኘው ድረ-ገጽ ገብታችሁ ፊርማችሁን በማስፈር ላገራችሁና ለወገኖቻችሁ ስትሉ ድጋፋችሁን በማበርከት በአቤቱታው እንድትተባበሩን በአክብሮት ይጠይቃል። የአቤቱታው ቅጂ፣ እንዳስፈላጊነቱ ተስተካክሎ፣ ለአሜሪቃ ፕሬዚደንት [USA President]፣ ለአውሮጳ አንድነት ሸንጐና[European Union Parliament] ለአውሮጳ አንድነት የሰብኣዊ መብቶች ጉዳይ ወኪል [European Union Commission for Human Rights] ይላካል። ቅጹን አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በሚከተለው መልክ እንድትሞሉት በጥብቅ እናሳስባለን ።
Sign this petition [እውነተኛ ሳይሆን ለምሳሌነት/ለናሙና ብቻ የተሰጠ]
Full Name፡ [Dr., Professor etc ] Gabremaryam Paulos, [PhD, JD,MD etc] ማዕርግዎን እንዳስፈላጊነቱ ከፊት ወይንም ከኋላ ያስገቡት ። ]
Location: University of Manchester, UK [ያገር ስም ሳይሆን፣ የሥራዎን ድርጅት/ተቋምና ያለበት ቦታ/አ ገር ።]
Email : gpaulos@manchester.edu [የ ድርጅት ዎን/ የ ተቋምዎን ኢሜይል ቢያስገቡ ይመረጣል ።]
ማሳሰቢያ። ከነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ባንዱም ላይ ማለትም ስምዎና ማዕርግዎ፣ የሥራዎ ቦታና ተቋም፣ እንዲሁም ኢሜይል ስሕተት ወይንም ሐሰት ሁኖ ቢገኝ ወይንም ጥርጣሬ ካለባቸው የአቤቱታ አቀነባባሪ ኮሚቴው ፊርማውን  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድረ-ገጹ አድራሻ እንደሚከተለው ነው።
http://www.petitionbuzz.com/petitions/appeal-to-the-un-secretary-general

No comments:

Post a Comment