Sunday, August 28, 2016

የኢሕአዴግ የተሃድሶ ጥሪ ማዘናጊያ እና የለውጥ ትግል መግደያ ነው። በተሃድሶ ስም አዲስ በጀት መድበው ለመዝረፍ ኣሰፍስፈዋል።


 የሕዝብ ችግር ኢሕአዴግና ፖሊሲው እንጂ መግለጫ እና የምክር ቤት ውሳኔ ኣይደለም ።መፍትሄው ስልታን ለሕዝብ ማስረከብ ብቻ ነው። የወያኔ መግለጫ (በማር የተለወሰ መርዝ)የሕዝብ ትግል ስላሽመደመደው በለመደው የውሸት መግለጫው ሕዝብን እያታለለ ለመኖር እንጂ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ መግለጫው በራሱ ምስክር ነው።በልማት እና በተሃድሶ ስም በመነገድ ላይ የሚገኘው ወያኔ የሕዝብን ትግል ለማኮላሸት የሚያደርገውን ማዘናጊያ እነ የሃሰት መግለጫውን ሳንሰማ እግላችንን ኣቀጣጥለን መቀጠል ኣለብን።
‹‹ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ መንፈስና ጉልበት ተጠናክረን እንመጣለን፤›› የሚለው ወያኔ ሕዝብን ለመፍጀት ራሱን በማጠናከር ላይ መሆኑን እየነገረን ነው ስለዚህ ሳይቀድሙን በመቅደም ድምጥማጣቸውን ልናጠፋው ይገባል፤ እንደገና በኣዲስ ኣመት ኣዲስ መንግስት ለማቋቋም የሚያስበው ወያኔ መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች ኣይነት ሆኖበታል፤ወያኔ ራሱ በሚፈጥረው ሽብርና በራሱ ፍርሃት ራሱ በሚሰራው ወንጀል የውጭም ሆነ የውስጥ ጽንፈኛ፣ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ኃይሎች በማለት መወንጀሉን ተያይዞታል።
የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ ሕገመንግስቱ መሰረት ኣድርጎ የትግራይ ክልል ሊፈታው ይገባል በማለት ጉዳዩን ለጨፍጫፊዎቹ ሕወሓቶች በመስጠት ብ አዴንን ደካም ድርጅት ሲል ፈርጆታል። የወልቃት ጉዳይ በኣስቸኳይ መፍጤ ኣግኝቶ የሕዝብ ጥያቄ ካልተመለሰ ትግሉ እንደተቀጣጠለ ይቀጥላል፥ የኣማራው ክልል የሕዝብ ብሶት የፈነዳው የወልቃይትን ጥያቄ ተከትሎ መሆኑን ለማመን ያልፈለገው ወያኔ ኣሁንም የወልቃይትን ጉዳይ ከሕወሓት ጉያ ለመምዘዝ ኣልፈለገም ሕወሓት በጉያዋ እሳት እንደታቀፈች ልታውቅ ይገባታል፤ወልቃይት ኣማራ ኢትዮጵያዊ ነው። ሰበበኛው ወያኔ የሚሰጠው መግለጫ የሚያደርገው ድርድር ሁሉ ሕዝብን ለማዘናጋት የለውጡን ትግል ለመግደል የሚሰራው ሴራ ኣንዱ አካል ነው።በተሃድሶ ስም አዲስ በጀት መድበው ለመዝረፍ ኣሰፍስፈዋል።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በየኣቅጠጫው የጀመረውን ትግል በመቀጠል በወያኔ መግለጫ ሳይዘናጋ በጀመረው የለውጥ ጉዞ ወያኔን ወደ ከርሰ መቃብሩ የመክተት የዜግነት ግዴታ ኣለብን፤ ድል የሰፊው ሕዝብ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ
Image may contain: text

No comments:

Post a Comment