ከሶስት አመታት በፊት ከተወሰኑ የተከበሩ ኢትዮጵያዉያን ጋር አንድ ኮሚቴ አቋቋምን። በ2007 ምርጫ፣ ደም ሳይፈስ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የፖለቲካ ልዩነቶች እንዲፈቱ ከወዲሁ ኢሕአዴግ እና ተቃዋሚዎች የድርሻቸዉን እንዲወጡ ለማግባባት። በ1997 የነበረው አይነትም ደም መፋሰስ እንዳይኖር። ብዙ ተሞከረ፣ ብዙ ተደከመ። ከተቃዋሚዎች ዘንድ ሙሉ ፍቃደኝነት ነበር።
ነገር ግን በሕወሃት/ኢሕአዴግ በኩል ግን በቃል ጥረታችን ጥሩ እንደሆነ ከመግለጽ ዉጭ ለዉይይት በተግባር ፍቃደኝነት አላሳዩም። በድርጅት ደረጃ አፍራሽ የሆኑ ተግባራትን መፈጸም ጀመሩ። ከዚህ ኮሚቴ መካከል የተወሰኑ፣ ለማግባባት ሥራ፣ ወደ ኢትዮጵያ ሄዱ። የኮሚቴው አባላት በኢትዮጵያ እያሉ፣ ከመድረክ አብርሃ ደስታ፣ ከአንድነት ዳነል ሺበሺና ሃብታሙ አያሌው፣ ከሰማያዊ የሽዋስ አሰፋ እንዲሆም ሌሎች በርካቶች “ሽብርተኞች ናችሁ” በሚል ታሰሩ። እነ እስክደርንን አንዱዋለም አራጌን እስናፈታለን ስንል ሌሎች ታሰሩ።
ብዙም አልቆየም ምርጫው ከመደረጉ አራት ወራት በፊት ጠንካራ የሆነውን የአንድነት ፓርቲን በፖለቲካ ዉሳኔ አገዱ። ጥረታችን ድካማችን በሙሉ መና ቀበሩት ማለት ይችላል።
አላማችን በምርጫው ቢያንስ የ97ቱን አይነት በአንጻራዊነት ዴሞክራሲያዊ የሆነ ምርጫ ተደርጎ፣ የፖለቲካ ማሻሻያዎች ታይተው ሁላችንም እንደ ሕዝብ አገራችንን በፍቅር መገንባቱ ላይ እናተኩራለን የሚል ነበር። ጭራሹኑ ግን ሞቶ በሞቶ አሸነፍን ብለው የሰላሙን በር ሙሉ ለሙሉ ዘጉት።
“የሰላም በር ሲዘጋ የአመጽ በሮች ይከፈታሉ” እንዳለው አብሃ ደስታ፣ ምርጫው ከተደረግ ከስድስት ወራት በኋላ በኦሮሚያ የኦሮሞዎች ተቃዉሞ ተጀመረ። ይኸው ዘጠኝ ወራት ሆነው። በተለይም በምራብ ሸዋ፣ በወለጋ፣ በምራብ አርሲና በሐረረጌ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞ ይሰማ ጀመር። በአማራው ክልል የአማራው ተጋድሎ በሚል፣ በጎንደር እና በጎጃም በመልኩና በአይነቱ ከኦሮሞው ተቃዉሞ የተለየ እንቅስቃሴ ተጀመረ።
በኦሮሚያ ላለፉት ሶስት ወራት፣ ቢያንስ ከዘጠኝ መቶ በላይ፣ ኦሮሞ ኢትዮጱያዉይን በአጋዚ ጦር ተገድለዋል። በአማራው ክልል ላለፉት አንድ ወር ብቻ ቢያንስ ከመቶ በላይ ከህዝብ ወገን ህይወታቸው ሲጠፋ ከአጋዚ ወገን ደግሞ ሁለት ወይንም ሶስት እጠፍ የሚሆን በህዝብ ታጣቂዎች ወድቀዋል።
በኦሮሚያ ላለፉት ሶስት ወራት፣ ቢያንስ ከዘጠኝ መቶ በላይ፣ ኦሮሞ ኢትዮጱያዉይን በአጋዚ ጦር ተገድለዋል። በአማራው ክልል ላለፉት አንድ ወር ብቻ ቢያንስ ከመቶ በላይ ከህዝብ ወገን ህይወታቸው ሲጠፋ ከአጋዚ ወገን ደግሞ ሁለት ወይንም ሶስት እጠፍ የሚሆን በህዝብ ታጣቂዎች ወድቀዋል።
ዛሬ ተራው የወሎና የሸዋ ነበር። እነዚህን ክፍል ሃገራት የጦር አዉድማ ነበር የሚመስሉት። በቆቦ፣ በደሴ፣ በኮምቦልቻ በደብረ ብርሃን፣ በወልዲያ፣ በሸዋ ሮቢት…ምንም አይነት እንቅስቃሴ አልነበረም። ሁሉ ነገር ተዘግቶ ነበር። ብዙ ወጣቶች ሰለፎችን ለማጨናገፍ ታፍሰዋል።
አንዷ የወያኔ ካድሬ ” የወሎና የሸዋ ሕዝብ የነፍጠኖጭን ጥሩ ዉድ አደረገ” ብላ እንደጻፈችው፣ ወያኔዎች በወሎና በሸዋ እንደ ጎንደርና እና እንደ ጎጃም፣ ሕዝቡ በብዛት አለመውጣቱን እንደ “ድል” እየቆጠሩ በመፎከር ላይ ናቸው። ነገ፣ ተነገ ወዲያ …ምን ሊሆን እንደሚችል ካለመገንዘብ ። መቼም እንደ ዛሬ ሰዉ ከቤቱ እንዳይወጣ አያስገድዱትም !!!!….ያኔ ምን ሊያደረጉ ነው ? ? ? እንደዉም ዛሬ የወሰዱት እርምጃና ያደረጉት ደርጊት ከመቼዉም በላይ ነው ኩሩዎቹን ሸዋና ወሎን የሚያስቆጣው።
ከሶስት አመታት በፊት እኛን ቢሰሙን ኖሮ ፣ ያን አስተዋይ ቢሆኑ ኖሮ ይሄን ጊዜ ችግር ዉስጥ ባልገቡ ነበር።
ከዚህ በኋላ ምን ሊሆን እንደሚችል መተንበዩ አስቸጋሪ ነው። እኔ እነርሱን ብሆን ነገሮች ወደ ባሰ የከፋ ዴረጃ ሳይደርሱ፣ ተኩስ አቁም አውጄ፣ ያሉ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ፍቃደኛ እንደሆንኩ አወጃለሁ። ዛቻና ማስፈራራቴን አቆማለሁ። የታሰሩትን ሁሉ እፈታለሁ። አገርን ወደ ቀዉስ በማስገባቴ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም አደርጋለሁ። ግን ችግሩ እነርሱ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ እንስሳ የሚያስቡ ስለሆነ ፣ በጥጋብ ስለተሞላ፣ ራሳቸውን በራሳቸው ማፈራረሳቸው አይቀሬ ነው።
No comments:
Post a Comment