ጌታቸው ረዳ « በራሳቸው ተነሳሽነት » ህገ ወጥ እርምጃ የወሰዱ የፖሊስ አባላት ላይ መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ አሳወቀውናል ። በመጀመሪያ ህገ ወጥ እርምጃ የሚወስዱ ፖሊሶች እንዳሉ ማመንህ ጥሩ ነው ። በመቀጠል የዚህ አርፍተ ነገር ምንነት ምን ይመስላል ? በአዲስ መስመር እንደሚከተለው ላቅርበው ።
ጌታቸው ከአንድ ሳምንት በፊት « ሁለት እሳት እና ጭድ የሆኑ አካላቶች እንዴት አንድ ሆነው ሊሰሩ ይችላሉ » በማለት እየተበሳጨ ሲናገር ሰምተነዋል ። እነ ጌታቸው ረዳን በሚያስፈራ መልኩ ባይሆንም « ከ ሊፕ ሰርቪስ ባለፈ » የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች ( በአመራር ደረጃ ሳይሆን ) መሬት ላይ ያለው ህዝብ ።፥ ከበፊቱ በተሻለ መልኩም ቢሆን የጋራ ጠላታቸው ወያኔ መሆኑን ማወቃቸው « identify » ማድረጋቸው ፥ የወያኔን ግብአተ መሬት እደሚያፈጥነው እና የ ጡዘት ተፅዕኖ «spinning effect » ሊኖረው እንደሚችል ስለተረዱ ፥ የነዚህን ሁለት ንዑስ ብሄራት ያልተፃፈ የጋራ ስምምነት ለማክሸፍ የመጀመሪያው መንገድ ጥቂት የፖሊስ አባላትን ባልተገባ እርምጃ ከሶ ለፍርድ ማቅረብ ሆኖ አገኙት ። ስሌታቸውም መሰረት ሊያደርግ የሚችለው የሚከተሉትን ሃሳቦች ነው
1ኛ የኦሮሚያ ተቃውሞ በጎንደር እና ባህር ዳር ከተነሳው ተቃውሞ የተለየ ነው ብሎ ማለት
2ኛ ልዩነታቸው ህጋዊ መሰረቶች እንዲይዙ ማድረግ
በነዚህ ሁለት ሃስቦች ላይ የሚከተሉትን ሃሳቦች ነድፎ ተግባራዊ ማድረግ
1•1 የኦሮሚያው ተቃውሞ በመሳሪያ ያልታገዘ ከመሆኑ አንፃር የደረሰው የአካል እና የህይወት አደጋ ፥ በተወሰነ ደርረጃም ቢሆን የህገ ፖሊሶች ገደብ የለሽ የሃይል መጠቀም እንደሆነና ፥ በዚህም መንግስት እንዳዘነ ፥ ሰዎቹንም ለፍርድ ሂደት እንደሚያቀርብ ዶክመንተሪ መስራት ።
1•2 ይህንን ዶክመንተሪ ተከትሎ ፥ በዚህ በህገወጥ ግድያ ላይ የተሳተፉ ሰዎችን መርጦ መለየት ።
1•3 የተለዩት የፖልስ ሰራዊት አባላት በሙሉ ከአማራ ብሄር የተወለዱ እና ተገደው ህገ ወጥ እርምጃ የወሰዱ እንደሆኑ እንዲያምኑ ማስገደድ
1•4 በዚህም የኦሮሞ ህዝብን የገደለው አሁንም የቀድሞ ስርአት ናፋቂቆች ፥ በህገ መንግስቱ የማሉ ፤ ግን ደሞ ህግ እና ስርዓቱን ለመናድ የተነሱ መሆናቸውን መስበክ ። ይህንንም ተከትሎ በኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ዳግም የአማራ ጥላቻን መፀነስ ፥ በጥላቻ እሳት የለበሱ እሳት የጎረሱ የኦሮሞ ፌደራል ወታደሮችን መመልመል እና እነዚህን ሰዎች ብድራቸውን ይመስልሱ ዘንድ በአማራ ክልል ማሰማራት
2•1 በጎንደር እና በጎጃም የተካሄደው አመፅ በመሳሪያ የታገሰ ስለሆነ መንግስት የወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ እንደሆነ በአደባባይ መናገር ። ይህም በኦሮሚያ ይቅርታ ሲጠይቅ በአማራ ግን ፥ የአማራን ህዝብ በመክሰስ ለጥፋቱ ይቅርታ እንዲጠይቅ የማስገደድ እና የማዋረድ ስራ መስራት። በሂደቱ እንደ አዲስ በአማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች መሃከል « በግንዛቤ ደረጃም ቢሆን » እየታየ ያለውን የጋራ ጠላትን ነጥሎ የመለየት ነገር ማደፍረስ ። ይህ እኔን የሚመስለኝ ነው ።
ፈረንጆቹ «To matter forever, you need to matter to those who don't care about you». የሚሉት ነገር አለ ። ወያኔም ለዘላለም ለመግዛት ፥ ወያኔ በቃኝ ላለው የኦሮሞ ህዝብ ራሱ ገሎ ፥ ግድያውን የጥቂት ፖሊስ አባላት ድርጊት አድርጎ መምጣቱ « ያዲያቆነ ሰይጣን » የሚለውን የአባቶች ብሂል የሚያስታውስ ነው ።
መደምደሚያ
ወያኔ ትግሬ የሚገባው ይቅርታ የ ሽንፈት ይቅርታ ብቻ ነው !
ኄኖክ የሺጥላ
No comments:
Post a Comment