Wednesday, August 31, 2016

በወቅቱ የሃገራችን ሁኔታ የተነሳ የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም የሚወጣበት ቀን ተሰረዘ በወቅቱ ሁኔታ ላይ ነጠላ ዜማ ሊለቅ ነው

(ዘ-ሐበሻ) ለአዲሱ ዓመት ይወጣል ተብሎ የነበረው የቴዲ አፍሮ አዲስ የሙዚቃ አልበም በሃገር ቤት በርካታ ሰዎች እየተገደሉ ባለበት በዚህ ወቅት እንዳይወጣ መደረጉ ተሰማ:: የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ቴዲ አፍሮ ሰው እየሞተ የሙዚቃ አልበሜን አላወጣም ብሏል::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ቴዲ አፍሮ በወቅቱ የሃገራችን ሁኔታ በቅርብ ቀን ውስጥ ነጠላ ዜማ እንደሚለቅ ታውቋል:: ይህ ነጠላ ዜማ ከአዲሱ ዓመት በፊት እንደሚወጣ ተሰምቷል::
አዲሱን ዓመት በማስመልከት ሊደረጉ ከነበሩ ኮንሰርቶች መካከል ሰው እየሞተ ኮንሰርት አልሰራም በሚል ማዲንጎ አፈወርቅ በአሜሪካ ሊያደራግቸው የነበሩትን ኮንሰርቶቹን መሰረዙ ይታወሳል:: ሌሎች ድምጻውያንም ይሰርዛሉ እየተባለ እየተጠበቀ ነው:

No comments:

Post a Comment