በቀድሞው በጌምድር በአሁኖቹ የሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እና ወልቃይት ጠገዴ፣ ከትላልቅ ከተሞች፣ ከጎንደር፣ ከደብረ ታቦር፣ ከደባርቅ ጀመሮ እስከ ትናንሽ የገጠር መንደሮች ሕዝቡ ምሬቱን ተቃዉሞው በትልቅ ድፍረትና ወኔ እየገለጸ ነው። ወልቃይት ጠገዴ ወደ ጎንደር ዞን እንዲጠቃለል፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱን ጨመሮ የታሰሩ ወልቃይት ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ የጥቂት የሕወሃት አባላት አምባገነናዊ አገዛዝ እንዲቆም. እኩልነት፣ ፍትህ እንዲሰፍን ህዝቡ እየጠየቀ ነው።
ሕወሃቶች የሕዥቡን ጥያቄ ለማ፣ፈን፣ ህዝቡን ለማስፈራራት ብዙ ሞከረዋል። ብዙ ሰላማዊ ዜጎንች ገድለዋል።፡ሆኖም ግን በሚያስገረም ሁኔታ የሕዝቡ ተቃዉሞ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው። ከዚህ በኋላ ነጻነቱን ካላገኘ በቀር የጎንደር ህጅዝብ ወደ ኋላ አይመለስም።
ከዚህ ቀጥሎ በጎንደር ስላለው ሁኔታ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ፣ ኢሳት እንዲሁም ሌሎች ከዘገቡት እኔም ከአካባቢው ካገኘሁት መረጃዎች አሰባስቢ አቅርቢያለሁ። መልካም ንባብ፡
ማክሰኚት፣ ገደብዬ እና ኢንፍራንስ
=====-============
=====-============
ሕዝባዊ እንቅስቃሴና ተቃዉሞ በሰሜን ጎንደር ዞን ማክሰኚት ከተማ በድጋሚ ተቀስቅሷል።
በማክሰኚት፡በገደብዬ፡በኢንፍራንዝ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። በአብደራፊ ግጭት አለ። መንገዶች ተዘግተዋል። ከአሸሬ ወደ ጎንደር የሚወስደው የሁመራ መስመር በአርማጮህ ህዝብ ተዘግቷል
በማክሰኚት፡በገደብዬ፡በኢንፍራንዝ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። በአብደራፊ ግጭት አለ። መንገዶች ተዘግተዋል። ከአሸሬ ወደ ጎንደር የሚወስደው የሁመራ መስመር በአርማጮህ ህዝብ ተዘግቷል
ዳባት እና ደባርቅ
=========
=========
የጎድነር ከተማን በመከተል የሥራ ማቆም አድማ ቀጥሏል።
አብደራፊ. አብርሃጅራ (ምእራብ አርማጭሆ)
=====
=====
በምዕራብ አርማጭሆ በአብደራፊና አብርሃጂራ መካከል በምትገኘው ኮርደምተሌ በምትባል ቦታ በፓትሮል የነበሩ የትግራይ ልዩ ሃይል ፖሊሶች አቶ ታያቸው የሚባሉ የአብርሃጂራ ባለሃብትን መግደላቸዉን ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ ከትግራይ ልዩ ሃይል ፖሊሶች ጋር ተኩስ እንደጀመረ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። ፖሊሶቹ ወደ ጫካ የተሸሸጉ ሲሆን ህዝቡ ጫካዉን ከቦ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል። በመራብ አርማጭሆ ዉጥረት አለ።
ደብረ ታቦር
=======
=======
በደብረ ታቦር ከተማ ከነሃሴ 22 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀን የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ እንደሚደረግ መርሃ ግብሩ ያሳያል፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እንዳትወጡ የሚሉ ማስታዎቂያዎች ተለጥፈዋል፡፡ ይህን ተላልፎ በሚገኝ ሰው ላይም የዐማራውን ተጋድሎ እንደመተላለፍ ስለሚቆጠር ከህዝብ ጋር እንደተጣላ ይቆጠራል ተብሏል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ቅጥረኛ ካቢኒዎች ነጋዴዎችን ሱቆቻቸውን እንዳይዘጉ ያስጠነቀቀ ሲሆን የቤት ውስጥ ተጋድሎው አስተባባሪዎች ማንኛውንም ተቋም የሚከፍት ሰው ከወያኔዎቸ ጋር እንዳበረ ስለሚቆጠር የሚያስከፍለው ዋጋ የከፋ ነው ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ጎንደር ከተማ
========
========
ጎንደር የቤት ውስጥ አድማው ለሦስተኛ ቀን ቀጥሏል፡፡ የቤት ውስጥ አድማው እስከ እሁድ ይደርሳል ተብሏል፡፡ ኮሎኔል ደመቀን የመውሰድ እቅዱ ከሽፏል።
የጎንደር ከተማ ልዩ ኃይል ፖሊስ ምክትል አዛዥ መልካሙ የሽዋስ ጋርም ብዛት ያላቸው የፖሊስ አባላት በወያኔ ትእዛዝ መቀነሳቸውን ሰምተናል፡፡ የተቀነሱት የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት በሕዝብ ላይ ባለመተኮሳቸው ነው የተባለ ሲሆን ሁሉም የዐማራ ፖሊሶች በዐማራው ሕዝብ ላይ እንደማይተኩሱ ቃል ገብተዋል ሲሉ ምንጮቻችን ነግረውናል፡፡
አዲረመጥ
=====
=====
በወልቃይት ከተማ አዲረመጥ ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የወልቃይት ዐማሮች የፋሲል ደመወዝን ‹‹ዐማራ ነኝ›› አዲስ ሙዚቃ ከፍተው ሲያዳምጡ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ‹‹አማርኛ ሙዚቃ ማዳመጥ አትችሉም›› በማለቱ በተፈጠረ ግጭት ከስድስት በላይ የሚሆኑ ፖሊሶች በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለው አምልጠዋል፡፡ አንድ የወልቃይት ዐማራ በጥይት የተመታ ሲሆን ለሕይወቱ አስጊ እንዳልሆነ ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
No comments:
Post a Comment