Wednesday, August 24, 2016

ለሁለተኛ ጊዜ የጎንደር ሕዝብ ቤቱን ዘግቶ ተቀመጠ – የወያኔ የኣደባባይ ተቃውሞ ጥሪ ከሽፏል።ጎጃም ፍኖተ ሰላም ታላቅ የተቃውሞ ትእይንት እየተካሄደ ነው


ለሁለተኛ ጊዜ የጎንደር ሕዝብ ቤቱን ዘግቶ ተቀመጠ – የወያኔ የኣደባባይ ተቃውሞ ጥሪ ከሽፏል።ጎጃም ፍኖተ ሰላም ታላቅ የተቃውሞ ትእይንት እየተካሄደ ነው::
 ሁለተኛው ዙር ኣድማ በጎንደር ከተማ ተጀምሯል የሚል መረጃ ከከተማዋ በስፋት ተሰራጭቷል፤ ኣሁን የጎንደር ሕዝብ የሕወሓት ጦር ከተማዋን ለቆ ካልወጣ ምንም ኣይነት ስራ እንደማይሰራ ቤት ውስጥ በመቀመጥ ኣድማ እንደሚያደርግ በተግባር እያሳየ ነው። ===  በምእራብ ጎጃም ዋና ከተማ ፍኖተ ሰላም ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ሲሆን ሕዝቡ የሕወሓትን ስርዓት በመቃውም ላይ ይገኛል።
በትላንትና እለት ሕዝቡ ኣደባባይ ወጥቶ የትግራይ ተወላጆችን እንዲገድል በከተማዋ የወያኔ ደህንነቶች ወረቀት ቢበትኑም በኣፋጣኝ በተወሰደው እርምጃ የወያኔ ሴራ መክሽፉ ታውቋል፤ ትላንትና በተለቀቀ መግለጫ አስቸኳይ መልእክት ለጎንደር ሕዝብ በሚል የወልቃይት ማንነት ኣስተባባሪ ኮሚቴ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረ የጎንደርን የሕዝብ እንቅስቃሴ ግብረሃይል ምንም ኣይነት ኣድማ ኣለመጥራቱንና የተጠራው ኣድማ የወያኔ ሴራ ስለሆነ የጎንደር ሕዝብ እንዳይቀበለው ኣሳስቧል። ሕዝብን ለማበጣበጥና ወያኔ የደም ጥማቱን ለማርካት የጠራው ኣመጽ ስለሆነ ማንም በዚህ የኣደባባይ ተቃውሞ ኣድማና ኣመጽ እንዳይሳተፍ ኣሳስበዋል።ወያኔ የጎንደር ሕዝብ በትግራይ ላይ ተነስ ብሎ ወረቀት በትኗል። እየተባለ ነው የማንነት ኣስተባባሪው ኮሚቴም ደግሞ እኛ ኣድማ ኣልጠራንም ማንም ሰው እንዳይወጣ መልእክቱን ኣድርሱልን ብለው ነበር። #ምንሊክሳልሳዊ
Image may contain: outdoor

No comments:

Post a Comment