Wednesday, August 31, 2016

ሕወሓት የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮ/ል አስራት በለጠን ከስልጣኑ አነሳ።


ሕወሓት የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮ/ል አስራት በለጠን ከስልጣኑ አነሳ።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮ/ል አስራት በለጠን ከስልጣኑ ማንሳቱ ታውቋል። ኮ/ል አስራት በለጠ ከስልጣኑ የተነሳው ባለፈው የደብረ ማርቆስ ሰልፍ በተካሄደበት ወቅት «አጋዚ አትላኩ የኛዎች ይበቃሉ፤ አጋዚ ከገደለ ጦርነቱ የሚሆነው ከእኛ ፖሊሶች ጋር ነው» ብሎ በመናገሩ ነው። እስካሁን ድረስ ግን በኮ/ል አስራት በለጠ ቦታ የተተካ ሰው የለም። የኮ/ል አስራት በለጠ መነሳትም ይፋ አልሆነም።
የኮ/ል አስራት በለጠን ከስልጣን መነሳት የሰሙ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነጋዴዎች  ኮ/ል አስራት በለጠ ለህዝብ በመወገኑ ተደስተው ወያኔ ለኮሎኔሉ ይከፍለው ከነበረው ደሞዝ በሶስት እጥፍ በመጨመር የነጋዴዎች ምክር ቤት ውስጥ በሀላፊነት ሊቀጥሩት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

No comments:

Post a Comment