በወለጋ መንዲ ከተማ መስቀልና መጽሐፍ ቅዱስ የያዙት ቄስ ቆስለው ታሰሩ
ቄስ ዳንኤል አብርሃም ይባላሉ፡፡የአገልግሎት ልብሳቸውን ለብሰው በአንድ እጃቸው መስቀል በአንደኛው መጽሐፍ ቅዱስ በመያዝ ባሳለፍነው ሳምንት በምዕራብ ኦሮሚያ ወለጋ ውስጥ በምትገኘው መንዲ ከተማ የሚገኙ ሰዎችን ከፊት እየመሩ ለፍትህ፣ለዕኩልነትና ለነጻነት አደባባይ ተገኙ፡፡
የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ቄሱንና የተከተላቸውን ህዝብ ለመበተን የሃይል እርምጃ በመውሰዳቸው የተወሰኑ ሰዎች ሲገደሉ ቄስ ዳንኤል ቆስለው በወታደሮች ወደ ወህኒ ቤት ተጋዙ፡፡እስካሁን ድረስም ምንም አይነት የህክምና እገዛ አለማግኘታቸው ታውቋል፡፡የነጻነት፣የፍትህና የዕኩልነትን ወንጌል ለምዕመናኖቻቸው በቃል ከማስማር አልፈው የህይወት ምስክርነት ለሰጡት ቄስ ዳንኤል ትልቅ አክብሮት እንሰጣለን፡፡

No comments:
Post a Comment