Thursday, August 11, 2016

የወያኔ ኣገዛዝ በከፍተኛ ውጥረት እና ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ሕዝብን ለማስፈራራት ቢሞክርም ኣልተሳካለትም።


የወያኔ ኣገዛዝ በከፍተኛ ውጥረት እና ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ሕዝብን ለማስፈራራት ቢሞክርም ኣልተሳካለትም። 
ነሀሴ 8 2008 የሕወሓትን አፓርታይድ አገዛዝ ለመገርሰስ በሚደረገው ርብርብ እንደ ጎንደር እና ባህርዳር ጎጃም ፣ሸዋና ወሎ የድርሻውን ሊወጣ ነው፥ በዚህም መሰረት በደብረብርሃን ፣በጎጃም ቅዳሜ ነሃሴ 7 2008 ዳንግላ ኮሶ በር ቡረ ፍኖተሰላም ደብረማርቆስ ሞጣ ቢቸና ደጀን ደብረወርቅና ግንደወይን ፡ እሁድ ነሃሴ 8 2008 በወሎ በመቄት በላስታ ላሊበላ በዋጎች ምድር ሰቆጣ ወልዲያ ራያ ዋድላና ደላንታ ደሴ ኮምቦልቻ ወልዲያ ሽዋሮቢት እና በኣከባቢው ወረዳዎች ከተሞች ታላቅ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፎች ለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል።
በደሴ በወልዲያ በኮምቦቻና በደብረብርሃን የወያኔ ኣባላት ሕዝቡ በነቀስ ወጥቶ የጎንደርና የባህርዳርትን ይደግመዋል በሚል ባደረባቸው ከባድ ፍራቻ ዛሬ በየከተሞቹ ጠዋት ባለሃብቶችን ከሰአት ደግሞ የባጃጅ ሾፌሮችን ወያኔ ሰብስቦ ቅዳሜ ሰልፍ ብትዎጡ አጋዚ አዘጋጅተናል ወዬላችሁ እያለ ሲያስፈራራ ነው የዋለው ። የባጃጅ ሾፌሮች አጉረምርመው እና የስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል።
ድል የሕዝብ ነው ያሉ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ለሆዳቸው ሳይገዙ ከባድ ትግል እያደረጉ መሆኑ ሲታወቅ በጉራጌ ክልል ነሃሴ ኣስረኣምስት ታላቅ ተቃውሞ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ድል የሕዝብ ነው!!! ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment