Sunday, August 28, 2016

በብዙ የዐማራ አካባቢዎች የመንግሥትን መዋቅር ሕዝቡ ተረክቧል፤ የጎበዝ አለቃዎች ጸጥታ የማስከበሩንና የመሪነት ሚናውን በሚገባ እየተወጡ ነው፡፡


መንግሥት ፈርሷል?! 
በብዙ የዐማራ አካባቢዎች የመንግሥትን መዋቅር ሕዝቡ ተረክቧል፤ የጎበዝ አለቃዎች ጸጥታ የማስከበሩንና የመሪነት ሚናውን በሚገባ እየተወጡ ነው፡፡ የአርባያ በለሳና የቋሪት አንበሶች ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ በድፍን ጎጃምና በድፍን ጎንደር ሕዝብ አገዛዙን አሽቀንጥሮ ለመጣል እየታገለ ነው፡፡ በወሎና በሸዋ ያሉ ዐማሮችም ተነስተዋል፡፡ ከ60 በመቶ በላይ በሚሆነው የዐማራ አካባቢ ወያኔ ለእግሩ መርገጫ የሚሆን ቦታ የለውም፤ ይህ ተጋድሎ በትንሽ ውጤት ሕዝቡ ሳይዘናጋ እስከ መጨረሻው መቀጠል አለበት፡፡ ዛሬ ያለው ግማሽ ድል ሙሉ እስኪሆን ድረስ ዐማራ ተጋድለውን ይቀጥላል፡፡ ዛሬ በተጋድሎ ያሉ ወንድሞቻችን ብዛት አይደለም አካባቢያቸውን ሁሉ ሙሉ በሙሉ መቁጠር አንችልም፤ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ገብደብየ፣ አምባጊወርጊስ፣ ጎንደር፣ ደምቢያ፣ አዲስ ዘመን፣በለሳ፣ ወረታ፣ ዓለም በር፣ ደብረ ታቦር፣ ጋሳይ- ክምር ድንጋይ፣ ነፋስ መውጫ፣ ሳሊ፣ ጨጭሆ፣ ጎብጎብ፣ ፍላቂት፣ ደራ ሐሙሲት፣ ባሕር ዳር፣ ፒኮሎ፣ ዱርቤቴ፣ አቸፈር፣ ዳንግላ፣ ቲሊሊ፣ ግምጃ ቤት፣ እንጅባራ፣ ቋሪት፣ ፍኖተ ሰላም፣ ብርሸለቆ- ጃቢጠናን፣ ቡሬ፣ ሽንዲ፣ ደምበጫ፣ የጨረቃ፣ አንበር፣ ሎማሜ፣ ፈረስ ቤት፣ አዴት ይልማና ዴንሳ፣ ጎንጅ ቆለላ፣ ሞጣ፣ ጉንደወይን…… በነዚህ ቦታዎች ሁሉ የዐማራ ሕዝብ ከወያኔ ጋር ግብግብ ነው፤ ለነጻነት ልጆቹን መስዋት እያደረገ ነው፡ በዚህ ሁሉ መካከል ግን ሊወሰዱ የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡ የዐማራው ሕዝብ መንግሥት መፍረሱን ተቀብሎ የሰላም ማስጠበቁን የመረከብ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ አዳዲስ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የጦር አበጋዞች መመረጥ አለባቸው፡፡ ሕዝቡ ደግሞ በመረጣቸው የጎበዝ አለቆች የመመራት ባሕሉን አጠናክሮ መሄድ አለበት፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ምርጥ መሪዎች ሕዝቡን ወደ ፊት ይዘው መሔዳቸውን እናያለን፤ የቋሪትና የበለሳ ተመክሮ እንደሚስፋፋ እሙን ነው፡፡
የዐማራው ገበሬ ለማይወክሉት የወያኔ ተላላኪዎች የመሬት ግብርና የማዳበሪያ፣ የአብቁተ ብድር ምናምን መክፈል የለበትም፡፡ ሁላችንም የዐማራ ልጆች ለገበሬ ዘመዶቻችን የማስረዳት ኃላፊነት አለብን፡፡ ሁሉም ገበሬ በየበቀበሌውና በየወረዳው አስተዳደር የሥልጣን እርከኖችን በልጆቹ የማስያዝ ሥራ አሁኑ መጀመር አለበት፡፡

በቀጣይ ቀናት ማናቸውም የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት በመላው የዐማራ አካባቢ እንደሚቋረጥ ይጠበቃል፡፡ የስልክና የኢንተርኔት መቋረጥ በውጭ ያለውን የአክቲቪዝም ሥራ የሚጎዳው ቢሆንም በአገር ውስጥ ያለውን ትግል ግን ወደ ኋላ አይመልሰውም፡፡
የዐማራ ሕዝብ የወያኔን ቂመኛነት ከማንም በላይ ያውቀዋል፤ በዚህም ወያኔ ይቅር ለእግዜር የሚባልበት የይቅርታ ዘመን አልፏል፡፡
የመጨረሻው መጀመሪያ እንዲህ ነው//
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

No comments:

Post a Comment